Go to full page →

ቤት ተጨባጭ ትምህርት የሚገኝበት ቦታ MYPAmh 212

የቤት ተልዕኮ ከቤተሰቡ አልፎ ወደ ሌሎች ይደርሳል:: የክርስቲያን ቤት የህይወትን እውነተኛ መርሆዎች ብቃት በመግለጥ ተጨባጭ ትምህርት መሆን አለበት። የዚህ አይነት መግለጫ በዓለም ውስጥ የመልካም ኃይል ይሆናል። እውነተኛ ቤት በሰብዓዊ ልቦችና ሕይወቶች የሚያሳድረው ተፅዕኖ ማንኛውም ሊሰበክ የሚችል ስብከት ከሚያሳድረው ተፅእኖ እጅግ የላቀ ነው። ወጣቶች ከእንደዚህ አይነት ቤቶች ሲወጡ የተማሩዋቸውን ትምህርቶች ለሌሎች ያጋራሉ። የከበረ የህይወት መርሆዎች ወደ ሌሎች ቤተሰቦች ይተላለፉና በህብረተሰቡ ውስጥ ከፍ የሚያደርግ ተፅእኖ ስራውን ይሰራል። Ministry of Healing, P. 352. MYPAmh 212.6