Go to full page →

የእናት ሽልማት MYPAmh 213

ፍርድ በሚሰየምበትና መጸሕፍት በሚከፈቱበት ጊዜ፣ ከታላቁ ፈራጅ አፍ “አንተ ታማኝ ባሪያ” የሚል ቃል ሲነገርና በአሸናፊው ግንባር ላይ ዘላለማዊ ክብር ያለው ዘውድ ሲጫን በተሰበሰቡ ብዙዎች አለማት ፊት ዘውዶቻቸውን በማንሳትና ወደ እናታቸው በመመልከት “በእግዚአብሔር ፀጋ አሁን የሆንኩትን እንድሆን አድርጋኛለች። እሷ የሰጠችኝ መመሪያዎችና ፀሎቶችም ለዘላለም ደህንነቴ በረከት ሆነውልኛል”ይላሉ። MYPAmh 213.4

ወጣቶች ጎልቶ እየታየ ባለው እርኩሰት ውስጥ ፀንተው እንዲቆሙ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል። ክፋት እየጨመረ እንዳይሄድ ለማገድ በእነርሱ አቅም ሊያደርጉ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉና መልካም ተግባርን፣ ንፅህናንና እውነተኛ ሰውነትን እንዲያጎለብቱ መሰልጠን አለባቸው። በህፃንነት ጊዜ የተፈጠሩ አሻራዎች ጥልቅና ዘለቄታ ያላቸው ናቸው። ትክክለኛ ያልሆኑ ስልጠናዎችና ክፉ ጓደኝነቶች ብዙ ጊዜ በወጣቶች አእምሮ ቆይተው ጥረት ቢደረግ እንኳን ሊፋቅ የማይችል የክፋት ተፅዕኖን ፈጥረው ያልፋሉ። The Signs of the Times, November 3, 1881. MYPAmh 213.5