Go to full page →

በቤት ውስጥ ስልጠና የመስጠት አጋጣሚዎች MYPAmh 213

የወደፊቱ ህብረተሰብ የሚወሰነው በዛሬው ልጆችና ወጣቶች ነው። እነዚህ ወጣቶችና ህፃናት ምን እንደሚሆኑ የሚወሰነው ደግሞ በቤት ውስጥ ነው። ሰብዓዊ ዘርን እየመታ ላለው የበሽታ፣ የስቃይና የወንጀል እርግማን መንሴኤዎች ትልቁን ድርሻ የሚወስደው በቤት ውስጥ ትክክለኛ ስልጠና አለመኖር ነው። የቤት ኑሮ ንፅህና እውነተኛ ቢሆን ኖሮና ከእነዚህ ቤቶች የሚወጡ ህፃናትም የህይወትን ሃላፊነቶችና አደጋዎች ለመጋፈጥ የተዘጋጁ ቢሆኑ ኖሮ በዓለም ላይ እንዴት ያለ ለውጥ በታየ ነበር:: The Ministry of Healing, P. 351. MYPAmh 213.6