Go to full page →

ለወላጆች ፍቅርና አክብሮት ማሳየት MYPAmh 215

ክርስቶስን በእውነት የሚከተሉት እርሱ በልባቸው እንዲያድርና የበላይ ሆኖ እንዲነግስ መፍቀድአለባቸው። በቤት ሕይወታቸው የእርሱን መንፈስና ባሕርይ መወከል አለባቸው። እንደዚሁምለሚያገኙአቸው ሰዎች ትህትናንና ደግነትን ማሳየት አለባቸው። MYPAmh 215.1

እውነትን እናውቃለን የሚሉ ግን ለወላጆቻቸው አክብሮትና ፍቅር የማያሳዩ ብዙ ልጆች አሉ።ለአባታቸውና ለእናታቸው ፍቅራቸው አነስተኛ የሆነ፣ ለፍላጎታቸው ግድ የለሽ በመሆን ወይም ከስጋትነፃ እንዲሆኑ ባለመሻት ተገቢውን አክብሮት የማይሰጡ ልጆች ብዙዎች ናቸው። ክርስቲያን ነን የሚሉብዙ ልጆች «አባትህንና እናትህን አክብር” ማለት ምን እንደሆነ አያውቁም፤ ከዚህም የተነሳ “እግዚአብሔር አምላክ በሚሰጥህ ምድር ላይ እድሜህ ይረዝም ዘንድ” የሚለው ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቁት እጅግ ጥቂት ነው። MYPAmh 215.2

ወጣቶቻችን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ከሚጠብቁ ህዝቦች መካከል ነን እያሉ ግን ብዙዎች አምስተኛውን ትዕዛዝ ችላ ይሉታል፣ ይጥሱታልም:: ከዚህም የተነሳ ይህንን ትዕዛዝ ለሚጠብቁና አባታቸውንና እናታቸውን ለሚያከብሩ የተገባው የበረከት ተስፋ ለእነርሱ ተፈፃሚ መሆን አይችልም። ኃጢአታቸውን ካልተናዘዙና ልምምዳቸውንና ባሕርያቸውን በክርስቶስ ፀጋ ካልለወጡ በስተቀር ለዘላለም ወደሚኖሩበት ወደ አዲሲቷ ምድር በፍፁም አይገቡም። ወላጆቻቸውን የማይወዱና የማያከብሩ እግዚአብሔርን አይወዱትም፣ አያከብሩትምም። ፈተናውን መሸከም የማይችሉ፣ እግዚአብሔርን የማይፈሩ፣ ወላጆቻቸውን የማያከብሩ፣ እግዚአብሔርን አይታዘዙትም፤ ስለዚህ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመምጣት ተስፋ ማድረግ አይችሉም። MYPAmh 215.3