Go to full page →

ወላጆችን ማስደሰት MYPAmh 217

ክርስቲያን የሆኑ ልጆች ከማንኛውም ምድራዊ በረከት ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወላጆቻቸውን ፍቅርና ማረጋገጫ ይመርጣሉ፡፡ ወላጆቻቸውን ይወዳሉ፣ ያከብራሉም፡፡ ወላጆቻቸውን እንዴት ማስደሰት እንደሚችሉ ማጥናት ከሕይወታቸው ዋና ዋና ጥናቶች አንዱ መሆን አለበት፡፡ በዚህ አመጸኛ ዘመን ትክክለኛውን ስልጠናና እርማት ያላገኙ ልጆች ለወላጆቻቸው ስላላቸው ግዴታ አነስተኛ ስሜት ይኖራቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ እንደሚታየው ወላጆቻቸው ለእነርሱ የበለጠ ባደረጉላቸው መጠን እነርሱ ደግሞ የበለጠ ምስጋና ቢሶችና አክብሮት የሌላቸው ናቸው፡፡ MYPAmh 217.3

ብዙ ጊዜ እሹሩሩ የተባሉና ከመጠን ያለፈ እንክብካቤ የተደረገላቸው ሁሉ ጊዜ ያንኑ ይጠብቃሉ፡፡ ያን የጠበቁትን ሳያገኙ ሲቀሩ ያዝናሉ፣ ተስፋም ይቆርጣሉ፡፡ ይህ ዓይነት አመለካከት በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ይታያል፡፡ ከዚህ የተነሣ ደካሞች፣ ሁል ጊዜ የሌሎችን እርዳታ የሚሹ፣ ሌሎች ውለታ እንዲውሉላቸውና እንዲሸነፉላቸው የሚፈልጉ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ወደ ሙሉ ወንድነትና ሴትነት ካደጉም በኋላ ተቃውሞ ከገጠማቸው እንደተበደሉ የሚቆጥሩ ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም በዓለም ውስጥ መንገዳቸውን በሐዘን ይሞሉታል፡፡ የራሳቸውን ክብደት መሸከም የማይችሉ ይሆናሉ፣ ሁሉም ነገር ስላልተመቻቸላቸው በተደጋጋሚ የሚያጉረመርሙና የሚያማርሩ ይሆናሉ፡፡ MYPAmh 217.4

ልጆች በህፃንነት ለተጠነቀቁላቸውና በታመሙ ጊዜ ላስታመሙአቸው ወላጆቻቸው የባለእዳነት (የባለውለታነት) ስሜት ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ወላጆቻቸው በእነርሱ ምክንያት ብዙ መከራና ጭንቀት እንደደረሰባቸው መገንዘብ አለባቸው፡፡ በተለይ ደግሞ እግዚአብሔርን የሚፈሩና ህሊና ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸውን ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ ጥልቅ ፍላጎት ተሰምቷቸዋል፡፡ በልጆቻቸው ላይ ስህተቶችን ሲያዩ ልባቸው እጅግ ይከብድ ነበር፡፡ ይህንን የልብ ሐዘን ያስከተሉ ልጆች የድርጊታቸውን ውጤት ማየት ቢችሉ ኖሮ በእርግጠኝነት ከስህተታቸው ይቆጠቡ ነበር፡፡ የእናታቸውን እንባ ማየት ቢችሉና ለእነርሱ ወደ እግዚአብሔር የጸለየቻቸውን ጸሎቶች፣ የታመቁና የሚቆራረጡ የሐዘን ሲቃዎችን መስማት ቢችሉ ኖሮ ልቦቻቸው አዝነው በፍጥነት ኃጢአቶቻቸውን በመናዘዝ ከእግዚአብሔር ይቅርታን ይለምኑ ነበር…፡፡ MYPAmh 217.5