Go to full page →

ለተጋድሎው ብርታት MYPAmh 218

ለሕፃናት ባልታደለ ዘመን ውስጥ እየኖርን ነን፡፡ ወደ ጥፋት የሚያመራ ከባድ ሞገድ እየመጠ ስለሆነ ይህንን ሞገድ ለመቋቋምና በእርሱ ከመወሰድ ለመዳን ከሕፃንነት ልምምድ የበለጠ ልምምድና ጥንካሬ ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ ወጣቶች የሰይጣን ምርኮኞች ይመስላሉ፤ እርሱና መላእክቱ እርግጠኛ ወደሆነ ጥፋት እየመሩአቸው ነው፡፡ ሰይጣንና ሰራዊቶቹ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየተዋጉ ናቸው፡፡ ልባቸውን ለእርሱ ለመስጠትና ትዕዛዙን ለመታዘዝ ፍላጎት ያላቸውን ሁሉ ተስፋ እንዲቆርጡና በጦርነቱ እጅ እንዲሰጡ ለማድረግ ሰይጣን ግራ ሊያጋባቸውና በፈተናዎቹ ሊያሸንፋቸው ይሞክራል…፡፡ MYPAmh 218.1

ልባዊ በሆነ ጸሎትና ሕያው እምነት ታላላቅ ድሎች ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ወላጆች በለያቸው ያለውን ኃላፊነት ባለመገንዘብ የልጆቻቸውን መንፈሳዊ ትምህርት ችላ ብለዋል፡፡ በማለዳ የክርስቲያን የመጀመሪያ ሀሳቡ በእግዚአብሔር ላይ መሆን አለበት፡፡ ዓለማዊ ሥራና የራስ ፍላጎት ሁለተኛ መሆን አለባቸው፡፡ ለሥራ ከቤት ከመውጣታቸው በፊት የቤተሰብ አባላት በሙሉ ተጠርተው አባት ወይም አባት በሌላ ጊዜ እናት በቀኑ ውስጥ እግዚአብሔር እንዲጠብቃቸው የጋለ ልመና መደረግ አለበት…፡፡ MYPAmh 218.2