Go to full page →

ውጫዊ መልክ MYPAmh 224

እግዚአብሔር ላደረገላችሁ ታላቅ መስዋዕትነት ምላሽ እንዲሆን አንድ ነገር ከእናንተ ይፈለጋል፡፡ ክርስቲያን እንድትሆኑ የሚፈልገው በስም ብቻ ሳይሆን በአለባበሳችሁና በንግግራችሁም ነው፡፡ በማያስፈልግ ብልጭልጭ፣ ላባዎችና ጌጣጌጥ ከማጌጥ ይልቅ ጨዋ አለባበስን በመልበስ የረካችሁ እንድትሆኑ ይፈልጋል፡፡ ባሕርያችሁን ሰማይ ማረጋገጫ ሊሰጠው የሚችል ዓይነት ማራኪ እንድታደርጉ ይፈልጋል፡፡ ውድ ወጣቶች ሆይ፣ MYPAmh 224.7

እርሱ የሚጠብቅባችሁን ሳትፈጽሙ በመቅራት ተስፋ ታስቆርጡት ይሆንን በውጭ የሚታየው ነገር አብዛኛውን ጊዜ የአእምሮ መግለጫ ስለሆነ ዓለም እምነታችንን እንዲመዝን ምን ዓይነት ምልክቶችን እያሳየን እንደሆነ መጠንቀቅ ያስፈልገናል፡፡ በሁሉም ነገር እግዚአብሔር ለገለጠልን ፈቃድ በመታዘዝ ኢየሱስን እንደ ውድ ልጆች እንድትከተሉት እንሻለን፡፡ ስለሆነም በየቀኑ በኢየሱስ እርዳታ ራሳችሁን ማሸነፍ ትችላላችሁ፡፡ ኩራትና የታይታ ፍቅር ከልባችሁና ከሕይወታችሁ ይወገዳል፡፡ የዋህነትና ትህትና ይደፋፈራሉ፡፡ ከዚህ የተነሣ ወጣቶች ለክርስቶስ ታማኝ ሰራዊትይሆናሉ፡፡ MYPAmh 224.8

እግዚአብሔርን እንደሚወዱና እንደሚታዘዙ የሚናገሩ ሰዎች በእለታዊ ሕይወታቸው እርሱን እየካዱ ባሉበት አደገኛ ጊዜ ውስጥ እየኖርን ነን፡፡ «ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፣ ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክህተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ፍቅር የሌላቸው፣ እርቅን የማይሰሙ፣ ሐሜታኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮ መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፡፡ MYPAmh 225.1

» ውድ ወጣቶች ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእነዚህ ሰዎች መካከል እንድትሆኑ አይፈልግም፡፡ ከእነዚህ ክፋቶችእንዴት መራቅ እንዳለባችሁና በመጨረሻ አሸናፊዎች መሆን እንደምትችሉ ከቃሉ መማር ትችላላችሁ፡፡ «በበጉ ደምና በምስክርነታቸው ቃል አሸነፉት፡፡” «በዚያን ጊዜም ጌታን የሚፈሩ አንዱ ለሌላው ተናገረ፣ ጌታም ሰማ፣ እርሱን ለሚፈሩትና ስሙን ለሚያስቡ በፊቱ የመታሰቢያ መጽሐፍ ተጻፈ፡፡» MYPAmh 225.2