Go to full page →

መመስከር MYPAmh 225

ከክፋት መራቅ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ከዚህ የበለጠ ማድረግ አለባችሁ፡፡ «መልካም ማድረግን መማር አለባችሁ፡፡” በዓለም ውስጥ ክርስቶስን መወከል አለባችሁ፡፡ እንዴት የእግዚአብሔርን ሥራ መስራት እንደምትችሉ መማር የየዕለቱ ትምህርት መሆን አለበት፡፡ የእርሱ ተከታዮች «በሰዎች ሁሉ የሚታወቁና የሚነበቡ” MYPAmh 225.3

ህያው ደብዳቤዎች መሆን አለባቸው፡፡ በምኞት ብቻ መልካም ባሕርይ ማግኘት አትችሉም፡፡ መልካም ባሕርይ የእናንተ መሆን የሚችለው ጥረት በማድረግ ነው፡፡ በዚህ አቅጣጫ ያለው ፍላጎታችሁ ልባዊ በሆነ እውነተኛ ሙከራና ትዕግሥት በተሞላበት ጥረት መገለጽ አለበት፡፡ በእድገት መሰላል ላይ በየቀኑ እርምጃዎችን በመሄድ በመጨረሻ በእርሱ በወደዳችሁ አሸናፊዎች፣ ከአሸናፊዎችም በላይ በመሆን ጫፍ ላይ ትደርሳላችሁ፡፡ The youth’s Instructor, November 5, 1896. MYPAmh 225.4