Go to full page →

የልብስ ጣዖት MYPAmh 232

የልብስ ጣዖት የግብረ ገብ በሽታ ነው። ይህ ጣዖት በክርስቶስ አዲስ ወደ ሆነው ሕይወት መተላለፍ የለበትም። በአብዛኛው ለወንጌል መስፈርቶች ራስን ማስገዛት በአለባበስ ፅኑ ለውጥን ይሻል። MYPAmh 232.1

በአለባበስ ግድ የለሽነት መኖር የለበትም:: ምስክሮች ስለሆንንለት ስለ ክርስቶስ ብለን አቀራረባችንን ከሁሉም የተሻለ ለማድረግ መጣር አለብን። በቤተ መቅደስ አገልግሎት በፊቱ የሚያገለግሉ ሰዎች ሊለብሱት ስለሚገባቸው የልብስ አይነቶች እግዚአብሔር እያንዳንዱን ነጥብ ዘርዝሮ ሰጥቷቸው ነበር። ለአሮን ልብሱ የሚወክለው ነገር ስለነበረው እጅግ ልዩ የሆነ መመሪያዎች ተሰጥተውት ነበር። እንደዚሁም የክርስቶስ ተከታዮች ልብስም ምሳሌያዊ ወይም ልዩ መሆናቸውን የሚወክል መሆን አለበት። በሁሉም ነገር የእርሱ ወኪሎች መሆን አለብን። በሁሉም አቅጣጫ ሰዎች የሚያዩን ገፅታችን የሚስብና ጨዋነትና ንፅህና ያለበት መሆን አለበት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ዓለምን ላለመምሰልበማለት ብቻ በልብሳችን አሰራር ላይ ምንም ለውጥ እንዳናደርግ ማዕቀብ አልጣለብንም። ክርስቲያኖች ማንነታቸውን ውድ በሆኑ ልብሶችና ጌጣጌጦች እንዳያስጌጡ ተከልክለዋል። MYPAmh 232.2

አለባበስን በተመለከተ የተፃፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በጥንቃቄ መታየት አለባቸው። አካላችንን ስናለብስ እንኳን የሰማይ ጌታ የሚወደውን አይነት አለባበስ ማወቅ ያስፈልገናል። የክርስቶስን ፀጋ ከልባቸው እየፈለጉ ያሉ ሁሉ በእግዚአብሔር የተሰጡትን ክቡር መመሪያዎች ያዳምጣሉ። የልብስ አይነት እንኳን የወንጌልን እውነት ይገልፃል:: Testimonies for the Church, Vol. 6, P. 96. MYPAmh 232.3