Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የልብስ ጣዖት

    የልብስ ጣዖት የግብረ ገብ በሽታ ነው። ይህ ጣዖት በክርስቶስ አዲስ ወደ ሆነው ሕይወት መተላለፍ የለበትም። በአብዛኛው ለወንጌል መስፈርቶች ራስን ማስገዛት በአለባበስ ፅኑ ለውጥን ይሻል። MYPAmh 232.1

    በአለባበስ ግድ የለሽነት መኖር የለበትም:: ምስክሮች ስለሆንንለት ስለ ክርስቶስ ብለን አቀራረባችንን ከሁሉም የተሻለ ለማድረግ መጣር አለብን። በቤተ መቅደስ አገልግሎት በፊቱ የሚያገለግሉ ሰዎች ሊለብሱት ስለሚገባቸው የልብስ አይነቶች እግዚአብሔር እያንዳንዱን ነጥብ ዘርዝሮ ሰጥቷቸው ነበር። ለአሮን ልብሱ የሚወክለው ነገር ስለነበረው እጅግ ልዩ የሆነ መመሪያዎች ተሰጥተውት ነበር። እንደዚሁም የክርስቶስ ተከታዮች ልብስም ምሳሌያዊ ወይም ልዩ መሆናቸውን የሚወክል መሆን አለበት። በሁሉም ነገር የእርሱ ወኪሎች መሆን አለብን። በሁሉም አቅጣጫ ሰዎች የሚያዩን ገፅታችን የሚስብና ጨዋነትና ንፅህና ያለበት መሆን አለበት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ዓለምን ላለመምሰልበማለት ብቻ በልብሳችን አሰራር ላይ ምንም ለውጥ እንዳናደርግ ማዕቀብ አልጣለብንም። ክርስቲያኖች ማንነታቸውን ውድ በሆኑ ልብሶችና ጌጣጌጦች እንዳያስጌጡ ተከልክለዋል።MYPAmh 232.2

    አለባበስን በተመለከተ የተፃፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በጥንቃቄ መታየት አለባቸው። አካላችንን ስናለብስ እንኳን የሰማይ ጌታ የሚወደውን አይነት አለባበስ ማወቅ ያስፈልገናል። የክርስቶስን ፀጋ ከልባቸው እየፈለጉ ያሉ ሁሉ በእግዚአብሔር የተሰጡትን ክቡር መመሪያዎች ያዳምጣሉ። የልብስ አይነት እንኳን የወንጌልን እውነት ይገልፃል:: Testimonies for the Church, Vol. 6, P. 96.MYPAmh 232.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents