Go to full page →

በሐይማኖት ውስጥ ያለ ደስታ MYPAmh 247

የቅዱሳን የወደፊት መኖሪያና ዘላለማዊ ሽልማት ወጣቶች ሊያሰላስሉባቸው የሚገቡ ከፍ ያሉና የከበሩ ጉዳዮች ናቸው። እናንተ በእርሱ ደም አማካኝነትና በመታዘዝ በመጨረሻ ወደ ክርስቶስ ዙፋን ከፍ እንድትሉ በተደረገው አስደናቂው የደህንነት እቅድና በክብር ንጉሥ በተፈፀመው መስዋዕትነት ላይ ሐሳባችሁን አድርጉ። ይህ ጉዳይ የአእምሮአችሁ የከበረ ማሰላሰያ ይሁን። በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት እንዴት ያለ መታደል ነው! MYPAmh 247.1

ወጣት ወዳጆች ሆይ፣ ይህንን በሚመስል ሥራና መዝናኛ ልትደሰቱ እንደምትችሉ አየሁ። ነገር ግን እናንተ እረፍት የለሾች የሆናችሁበት ምክንያት ብቸኛ የሆነውን •እውነተኛ የደስታ ምንጭ ስለማትፈልጉ ነው። በክርስቶስ ብቻ ሊገኝ የሚችለውን ደስታ ከእርሱ ውጭ ለማግኘት ሁልጊዜ እየጣራችሁ ነው። በእርሱ ሳይፈፀሙ የቀሩ ተስፋዎች የሉም:: ፀሎት፣ እነሆ ይህ የከበረ እድል እንዴት ችላ ተባለ! የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ አእምሮን ለፀሎት ያዘጋጃል። ወደ እግዚአብሔር በፀሎት ለመቅረብ አነስተኛ ዝንባሌ እንዲኖራችሁ ከሚያደርጉ ታላላቅ ምክንያቶች አንዱ ግምታችሁን በመቀስቀስና ያልተቀደሰ ፍላጎትን በማነሳሳት ለዚህ የተቀደሰ አገልግሎት ገጣሚ እንዳትሆኑ የሚያደርጉትን አስደሳች ታሪኮችን በማንበባችሁ ነው። ይህንን ስትለምዱ የእግዚአብሔር ቃል ጣእሙን ያጣና የፀሎት ሰዓት ይረሳል። ፀሎት የክርስቲያን ጥንካሬ (ብርታት) ነው። የሚፀልይ ክርስቲያን ብቻውን ሲሆን እንኳን ብቻውን አይደለም። “እነሆ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ::” ያለው ኢየሱስ አብሮት እንዳለ ይሰማዋል። MYPAmh 247.2

ወጣቶች የሌላቸውን ነገር ይፈልጋሉ፣ ያውም ኃይማኖት ነው። የዚህን ነገር ቦታ ምንም ነገር ሊተካ አይችልም። ኃይማኖት አለኝ ማለት ብቻውን ጥቅም የለውም። ስሞች በምድራዊው የቤተክርስቲያን መዝገብ ውስጥ ተመዝግበዋል፣ ነገር ግን በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ አልተመዘገቡም። ከወጣቶቻችን መካከል ከ20ዎቹ አንዱ እንኳን በተግባር የሚገለፅ ኃይማኖት ምን እንደሆነ እንደማያውቁ አየሁ። ራሳቸውን እያገለገሉ የክርስቶስ አገልጋዮች ነን ይላሉ። ነገር ግን በላያቸው ያለው አስማት ካልተወገደ በቀር የህግ ተላላፊ ዕጣ የእነርሱ መሆኑን በቅርቡ ይገነዘባሉ። ራስን መካድን ወይም ለእውነት መስዋእትነት መክፈልን በተመለከተ ከዚህ ሁሉ የተሻለ ቀላል መንገድ አግኝተዋል። የእግዚአብሔርን የምህረት ፀጋንና የሰይጣንን ፈተናዎች ለመቋቋም ጉልበት ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ብርቱ በሆነ እንባ ተግቶ በመፀለይ ፈንታ ይህንን ያህል ትጋትና ቅንዓት እንደማያስፈልግ ግንዛቤ ፈጥረዋል። እነዚህን ነገሮች ሲያደርጉም ያለ ችግር የክርስትና ሕይወት መምራት ይቻላል የሚል አቋም አላቸው። የክብር ንጉሥ የሆነው ክርስቶስ የነፍሱን ጥያቄ በአባቱ ፊት ለማፍሰስ ብዙ ጊዜ ብቻውን ወደ ተራራዎችና በረሃማ ቦታዎች ይሄድ ነበር። ነገር ግን በውስጡ ብርታት የሌለው ኃጢአተኛ ሰው ያለ ብዙ ፀሎት መኖር እንደሚችል ያስባል። Testimonies for the church, Vol. 1, P. 503-505. MYPAmh 247.3