Go to full page →

የኢየሱስ ምሳሌ MYPAmh 247

ኢየሱስ በራስ ደስታ መጠመድን በሁሉም መልኩ ገስፆታል፣ ሆኖም እርሱ በተፈጥሮው ማህበራዊ ሕይወትን ሚወድ ነበር። የሁሉንም የህብረተሰብ መደቦች መስተንግዶ ተቀብሏል! አስተሳሰባቸው ተራ ከሆኑ የህይወት ጥያቄዎች ወደ መንፈሳዊና ዘላለማዊ ነገሮች ለማንሳት በመሻት የድሆችንም ሆነ የሀብታሞችን፣ የምሁራንንም ሆነ የመሃይማንን ቤቶች ጎብኝቷል። ልቅ ለሆነ አኗኗር ምንም ፈቃድ አልሰጠም፣ ምንም ዓይነት ዓለማዊ ከንቱነት ባሕርዩን አላበላሸም! ሆኖም ክፋት በሌለባቸው የደስታ ቦታዎች ደስ ይሰኝ ነበር። በማህበራዊ ስብሰባዎች በመገኘትም እንደዚህ ዓይነት ክፋት የሌለባቸው ህብረቶች ጠቃሚ መሆናቸውን አረጋገጠ። Desire of Ages P. 150 -151. MYPAmh 247.4