Go to full page →

ማህበራዊ ስብሰባዎች MYPAmh 249

ለማህበራዊ ጉዳዮች የሚደረጉ ስብሰባዎች ተሰብሳቢዎቹ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባቸው ውስጥ እያደገ ያለ ሲሆንና ስለ እግዚአብሔር ቃል ሀሰብ ለመለዋወጥ ወይም ቃሉን ለማስፋፋትና ለመሰሎቻቸው መልካም ለማድረግ በሚሰበሰቡበት ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ትርፋማና አስተማሪ ናቸው። በእነዚህ ስብሰባዎች መንፈስ ቅዱስ እንዲገኝ በሚጋበዝበት ጊዜና እርሱን የሚያሳዝን ምንም ነገር በማይነገርበት ጊዜ እግዚአብሔር ይከብራል! ተሰብሳቢዎቹም ይታደሳሉ፣ ብርታትም ያገኛሉ። MYPAmh 249.1

ነገር ግን የተለየ ባሕርይ ያላቸው ማህበራዊ ስብሰባዎችም አሉ! በእነዚህ ስብሰባዎች ብዙ ጊዜ የመልክ ኩራት፣ ቧልትና ከንቱነት ይታይባቸዋል። ደስታን ለማግኘት ካላቸው ታላቅ ፍላጎት የተነሣ የስብሰባው ተሳታፊዎች እግዚአብሔርን የሚያስለቅሱ ነገሮች ያደርጋሉ። ለጊዜው የመደሰቻው ቦታ ገነት ይሆንላቸዋል። ሁሉም ራሳቸውን ለቧልትና ለፈንጠዚያ አሳልፈው ይሰጣሉ። ዓይኖች ይበራሉ፣ ጉንጭ ይቀላል፣ ነገር ግን ህሊና ይተኛል። MYPAmh 249.2