Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ማህበራዊ ስብሰባዎች

    ለማህበራዊ ጉዳዮች የሚደረጉ ስብሰባዎች ተሰብሳቢዎቹ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባቸው ውስጥ እያደገ ያለ ሲሆንና ስለ እግዚአብሔር ቃል ሀሰብ ለመለዋወጥ ወይም ቃሉን ለማስፋፋትና ለመሰሎቻቸው መልካም ለማድረግ በሚሰበሰቡበት ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ትርፋማና አስተማሪ ናቸው። በእነዚህ ስብሰባዎች መንፈስ ቅዱስ እንዲገኝ በሚጋበዝበት ጊዜና እርሱን የሚያሳዝን ምንም ነገር በማይነገርበት ጊዜ እግዚአብሔር ይከብራል! ተሰብሳቢዎቹም ይታደሳሉ፣ ብርታትም ያገኛሉ።MYPAmh 249.1

    ነገር ግን የተለየ ባሕርይ ያላቸው ማህበራዊ ስብሰባዎችም አሉ! በእነዚህ ስብሰባዎች ብዙ ጊዜ የመልክ ኩራት፣ ቧልትና ከንቱነት ይታይባቸዋል። ደስታን ለማግኘት ካላቸው ታላቅ ፍላጎት የተነሣ የስብሰባው ተሳታፊዎች እግዚአብሔርን የሚያስለቅሱ ነገሮች ያደርጋሉ። ለጊዜው የመደሰቻው ቦታ ገነት ይሆንላቸዋል። ሁሉም ራሳቸውን ለቧልትና ለፈንጠዚያ አሳልፈው ይሰጣሉ። ዓይኖች ይበራሉ፣ ጉንጭ ይቀላል፣ ነገር ግን ህሊና ይተኛል።MYPAmh 249.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents