በባሕርያቸውና በኃይማኖታዊ ልምምዳቸው አስመሳይ የሆኑ ለደሰታና ለፍስሀ ያለ አንዳች ችግር ስለሚሰበሰቡ የእነርሱ ተፅእኖ ሌሎችን ይስባል። አንዳንድ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ለመሆን እየጣሩ ያሉ ወንዶችና ሴቶች በእነዚህ ግብዣዎች እንዲሳተፉ ይደረጋሉ። ከሌሎች የተለዩ ለመሆን በላመፈለጋቸውና በተፈጥሮአቸው የሌሎችን ምሳሌ ለመከተል የሚያዘነብሉ ከመሆናቸው የተነሳ ምናልባትም በአእምሮአቸው ወይም በልባቸው መለኮታዊ ንካት ተሰምቷቸው በማያውቁ ሰዎች ተፅዕኖ ሥር ራሳቸውን ያስቀምጡ ይሆናል። በክርስቲያን ዛፍ ላይ ሊፈራ ስለሚገባው ፍሬ ክርስቶስን ምን እንዳለ ለማወቅ በፀሎት መለኮታዊውን መስፈርት መርምረው ቢሆን ኖሮ እነዚህ መዝናኛዎች ነፍሳት የበጉን ሰርግ ግብዣ እንዳይቀበሉ ለማድረግ የተዘጋጁ ግብዣዎች መሆናቸን ይገነዘቡ ነበር። MYPAmh 249.7
በእግዚአብሔር መንገድ በጥንቃቄ የተማሩ ወጣቶች አንዳንድ ጊዜ ወደ መደሰቻ ቦታዎች ደጋግሞ በመሄድና በሰዎች ተፅዕኖ ስበት በመወሰድ በትምህርታቸውና ሥልጠናቸው ዓለማዊ ባሕርይ ካላቸው ጋር ግንኙነት ይፈጥራሉ። ክርስቶስን መሰል ውበት ከሌላቸው ሰዎች ጋር ህብረት በመፍጠር ራሳቸውን ለእድሜ ልክ ባርነት ይሸጣሉ። እግዚአብሔርን በእውነት የሚወዱና የሚያገለግሉ ሰዎች ክርስቶስን በልባቸው ካላነገሱት ጋር ህብረት ለመፍጠር በመምረጥ ራሳቸውን ወደ ዓለም ደረጃ ዝቅ ለማድረግ ይፈራሉ። የሚከተሉት መንገድ ራስን መካድንና ራስን መስዋዕት ማድረግን የሚጠይቅ እንኳን ቢሆን በድፍረት ለክርስቶስ ይቆማሉ። MYPAmh 250.1