Go to full page →

ለደስታ ፍለጋ ከንቱነት መድሃኒቱ MYPAmh 250

ክርስቶስ ለእኛ ሲል የልፋትና የመስዋእትነት ሕይወት እስከኖረ ድረስ እኛ ለእርሱ ራሳችንን መካድ አንችልምን? እርሱ ለእኛ ያደረገው መስዋዕትነትና ሊሰጠን እየጠበቀ ያለው ጽድቁ አእምሮአችንን ለመያዝ በቂ የሆነ ዋጋ የለውምን? ወጣቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ግምጃ ቤት ውስጥ ያለውን ሀብት ማውጣት ቢችሉ ኖሮ፣ ራስን የመካድ ሕይወት ዘውድ የሆነውን ይቅርታ፣ ሰላምና የዘላለም ጽድቅን ቢያሰላስሉ ኖሮ ጥያቄ ለሚያሳድሩ የመደሰቻ ማነቃቂያዎች ፍላጎት አይኖራቸውም ነበር። MYPAmh 250.2

የወጣቶች ሐሳቦች ከፍ ባሉና የከበሩ የደህንነት ጉዳዮች ሲያዙ ኢየሱስ ደስ ይለዋል። ወደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች ልብ እንደሚቆይ እንግዳ በመግባት በደስታና በሰላም ይሞላቸዋል። በእነዚህ ነፍሳት ውስጥ የክርስቶስ ፍቅር “ለዘላለም ሕይወት እንደሚፈልቅ የህይወት ውኃ ምንጭ ነው::” ይህ ፍቅር ያላቸው ሰዎች እግዚአብሔር ለሚወዱት ስላዘጋጀው ነገር መናገር ደስታ ይሰጣቸዋል። MYPAmh 250.3

ዘላለማዊ የሆነ አምላክ በቅዱስና በኃጢአተኛ መካከል፣ በተለወጠና ባልተለወጠ መካከል መለያ መስመር አስምሯል። ሁለቱ ክፍሎች እንደ ቀስተ ደመና ቀለሞች መለየት እስከሚያቅት ድረስ አይደባለቁም፣ ነገር ግን እንደ እኩለ ቀንና •እንደ እኩለ ሌሊት ተለይተው ይታወቃሉ። የእግዚአብሔር ህዝቦች እውነትን እያወቁ በተግባር ከማይገልፁ ጋር ያለ አንዳች አደጋ ጥብቅ አንድነት አይፈጥሩም። አበው ያዕቆብ ስለ ልጆቹ አንዳንድ ድርጊቶች በፍርሃት እያሰላሰለ “ነፍሴ ሆይ ወደ ምክራቸው አትግቢ፣ ክብሬ ሆይ በጉባኤያቸውም አትተባበሪ” ብሏል። እርሱ ከኃጢአተኞች ጋር በድርጊታቸው ቢተባበር ኖሮ ክብሩም በተግባራቸው እንደሚተባበር ተሰማው። ከመጥፎ ህብረቶች እንድንርቅ የማስጠንቀቂያ ምልክትን ከፍ አድርጎ አሳየ! ያለበለዚያ በክፋት እንጎድፋለን። መንፈስ ቅዱስ በሐዋሪያው ጳውሎስ አማካኝነት “ፍሬ ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፣ ነገር ግን ገስፁአቸው።” ብሏል። The Youth’s Instructor, February 4, 1897. MYPAmh 250.4