Go to full page →

ልል የሆነ የአኗኗር መንገድ MYPAmh 255

በብዙ ሃይማኖተኛ ቤተሰቦች ውስጥ መደነስና ካርታ መጫወት የቤት ውስጥ ጊዜ ማሳለፊያዎች ሆነዋል። እነዚህ ጨዋታዎች ያለ ምንም አደጋ በወላጆች እይታ ውስጥ በመሆን የሚፈፀሙ ፀጥ ያሉና የቤት ውስጥ መደሰቻዎች ናቸው በማለት መከራከሪያ ይቀርብላቸዋል። ነገር ግን የእነዚህ ስሜትን የሚያነሳሱ መደሰቻዎች ፍቅር እያደገ ሲሄድ ያ በቤት ውስጥ ጉዳት የለሽ ተብሎ የነበረው ወጣ ሲባል ባሕርዩን ይቀይርና ጎጂ ሆኖ ይገኛል። ሆኖም ከእነዚህ መዝናኛዎች የሚገኝ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ ማረጋገጫ ሊሰጥ ይገባል። ለአካል ብርታትም ሆነ ለአእምሮ እረፍት አይሰጡም። በነፍስ ውስጥ አንድ በጎ ነገር ወይም ቅዱስ አስተሳሰብ አይተክሉም። በተቃራኒው ግን ትኩረት ለሚገባቸው ነገሮችና ለመንፈሳዊ አገልግሎቶች ያለውን ፍላጎት ያጠፋሉ። በተሻለ ደረጃ በሚመደቡ ምርጥ ግብዣዎችና በዳንስ ቤቶች በሚፈፀሙ የዝሙትና የውርደት ስብሰባዎች መካፈል ሰፋ ያለ ልዩነት መኖሩ እውነት ነው። ሆኖም ሁሉም ቢሆን ወደግብረ ገብ ልልነት የሚወስዱ እርምጃዎች ናቸው። MYPAmh 255.5

ዛሬ የሚፈፀሙ የዳንስ መዝናኛዎች የክፋት ትምህርት ቤቶችና ለማህበረሰቡ አስፈሪ እርግማኖች ናቸው። በአገራችን ባሉ ታላላቅ ከተማዎች ውስጥ በየዓመቱ እየጠፉ ያሉ ሰዎች አንድ ላይ ቢሰበሰቡ ኖሮ ምን ዓይነት ጎስቋላ ሕይወቶች ታሪክ ይታይ ነበር። እነዚህ ተግባራት ጎጂ እንዳልሆኑ ከሚናገሩት መካከል ስንቶቹ ውጤቱን ሲያዩ ሐዘንና መደነቅ ይይዛቸው ነበር። ክርስቲያን ነን የሚሉ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በእነዚህ አይነት ግበዣዎች ላይ በመገኘት ልጆቻቸውን በፈተና መንገድ ላይ ለማስቀመጥ እንዴት ይስማማሉ? ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች እንዴት ነፍሶቻቸውን ለዚህ የሞኝነት ደስታ ይለውጡታል? — The Review and Harold, Feb 28, 1882. MYPAmh 255.6