Go to full page →

የመዝናኛዎች አደጋ MYPAmh 256

የመደሰት ፍቅር በከተማዎች የሚኖሩ ልጆችንና ወጣቶችን ከሚያጠቁ ብዙ ፈተናዎች አንዱና ምስጢራዊ ከመሆኑ የተነሣ እጅግ አደገኛ ፈተና ነው። በዓላቶች ብዙ ናቸው! ጨዋታዎችና የፈረስ ግልቢያ ውድድሮች በሺዎች የሚቆጠሩትን ሰዎች ቀልብ ይስባሉ! ደስታን የመሻት አውሎ ነፋስ ረጋ ያሉ የህይወት ተግባራትን እንዳይፈፅሙ ይስባቸዋል። በአብዛኛው አጋጣሚዎች ድሆች እጅግ ለፍተው የሚያገኙት ትንሽ ገንዘብ ለተሻለ ጠቀሜታ ሊቀመጥ ሲችል ለዚህ መዝናኛ እንዲባክን ይደረጋል። MYPAmh 256.1