Go to full page →

ከንቱ መደሰቻዎች እውነተኛ ደሰታ አይደሉም MYPAmh 272

ከሌሎች ጋር አንድነት መፍጠርን የሚወዱ ሰዎች ብዙ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠራቸው ስሜት እስኪሆን ድረስ በከንቱ መደሰቻ ይጠመዳሉ። የህይወታቸው ዓላማ መልበስ፣ የመደሰቻ ቦታዎችን መጎብኘት፣ ከከንቱነትም ባነሱ ነገሮች ላይ መሳቅና ማውራት ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ሰማያዊ የሆኑ ነገሮችን ለማሰላሰል ትዕግስት የላቸውም። የሆነ የሚያነቃቃቸው ነገር ከሌለ በስተቀር ጎስቋላዎች ናቸው። ደስተኛ ሊያደርጋቸው የሚችል ኃይል በውስጣቸው የለም:: ነገር ግን ደስታን ለማግኘት ልክ እንደ እነርሱ ባሉ ሐሳብ የለሽና ግድ የለሽ የሆኑ ወጣቶች ጓደኝነት ይደገፋሉ። ለከበረ ዓላማ መዋል የሚችሉ ኃይሎችን ለሞኝነት አሳልፈው ይሰጣሉ…። MYPAmh 272.6

የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብና በፀሎት ሰዓት ደስታና ፍስሐን የሚያገኝ ወጣት ከሕይወት ውኃ ምንጭ በሚፈስ ውኃ ያለማቋረጥ ይታደሳል። ሌሎች ሊደርሱበት ወደማይችሉት ከፍተኛ የብቃት ደረጃና የአስተሳሰብ ስፋት ይደርሳል። ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት መልካም አስተሳሰቦችን፣ የከበሩ ፍላጎቶችን፣ እውነትን አጥርቶ ማየትን፣ ከፍ ያሉ የተግባር አላማዎችን ያደፋፍራል። ስለዚህ ነፍሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያቆራኙ ሰዎች የእርሱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንደሆኑ ይታወቃሉ። እነርሱ ጌታ ለዓለም የጥበብና የብርሃን መተላለፊያዎች እስከሚያደርጋቸው ድረስ የእግዚአብሔርንና የዘላለም ሕይወትን ግልጽ እይታ በማግኘት ከፍ ወዳለውና አሁንም ወደ ከፍታ እየደረሱ ናቸው። MYPAmh 273.1

በኢየሱስ የሚኖሩ በእግዚአብሔር የሚደሰቱና ሀሴት የሚያደርጉ ይሆናሉ። በድምፃቸው ራስን የማስገዛት ጨዋነት ይታያል፣ በተግባራቸው ለዘላለማዊና መንፈሳዊ ነገሮች አክብሮት ይታይበታል፣ ከንፈራቸው ሙዚቃ፣ ደስታ የተሞላበት ሙዚቃ ያስተጋባል! ይህም የሆነበት ምክንያት ከእግዚአብሔር ዙፋን የሚፈስ ስለሆነ ነው። ይህ በቀላሉ ለማብራራት የማይቻል ግን የሚሰማንና የምንደሰትበት የአምልኮ ምስጢር ነው። ትዕቢተኛና አመፀኛ የሆነ ልብ ጣፋጭ ለሆነው የእግዚአብሔር ፀጋና ለመንፈስ ቅዱስ ደስታ በሙሉ በሮቹን ይዘጋል። ነገር ግን የጥበብ መንገዶች የደስታ መንገዶችና መተላለፊያዎቿም በሙሉ ሰላም ናቸው። ከክርስቶስ ጋር የበለጠ በቅርበት በተቆራኘን ቁጥር ቃላቶቻችን የበለጠ ለእርሱ ፀጋ የመገዛትንና የፀጋውን የመለወጥ ኃይል ያሳያሉ። Testimonies for the Church, Vol. 4, P 622 -626. MYPAmh 273.2