Go to full page →

ሐይማኖተኛ ያልሆኑ እንግዶች MYPAmh 274

ለክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ከሌላቸውና ድርጊታቸው እግዚአብሔርን ከማያስደስት ሰዎች ጋር ጓደኝነት ለመፍጠር መምረጥ አደጋ አለበት። ነገር ግን ብዙ ክርስቲያን ነን ባዮች በዚህ የተከለከለ ግንኙነት ውስጥ በድፍረት ይገባሉ። ብዙዎች ከንቱ የሆኑ፣ አሿፊና እግዚአብሔርን የማያመልኩ ዘመዶቻቸውን ወደ ቤታቸው ይጋብዛሉ። ብዙ ጊዜ የእነዚህ ሐይማኖተኛ ያልሆኑ ጎብኝዎች ምሳሌና ተፅዕኖ በቤት ውስጥ ባሉ ህፃናት አእምሮ ዘለቄታ ያለው አሻራ አሳርፎ ያልፋል። እነዚህ ሰዎች የሚያሳድሩት ተፅዕኖ እብራውያን ከጣዖት አምላኪዎች ጋር ሲገናኙ ካስከተለው ውጤት ተመሳሳይ ነው። MYPAmh 274.1

ብዙዎች እግዚአብሔርን የማያምኑ ዘመዶቻቸውን ለማስደሰት በአንድንድ ነገሮች ላይ መደራደር እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። ሁልጊዜ መለያ መስመር ማስመር ቀላል ባለመሆኑ አንድ ድርድር ለሌላ መንገድ እየከፈተ ይሄድና በአንድ ወቅት እውነተኛ የክርስቶስ ተከታታዮች የነበሩ ግለሰቦች በሕይወትና በባሕርይ ለዓለም ወግ ተገዥ እሰከ መሆን ደረጃ ይደርሳሉ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጧል። በስም ብቻ ክርስቲያኖች ናቸው። የፈተና ጊዜ ሲመጣ ተስፋቸው መሰረት የሌለው መሆኑ ይታያል። ራሳቸውንና ልጆቻቸውን ለጠላት ሽጠዋል። እግዚአብሔርን አዋርደዋል! የእርሱ የጽድቅ ፍርድ በሚገለጥበት ቀን የዘሩትን ያጭዳሉ። ክርስቶስ ለጥንቱ እሥራኤላውያን እንዳለው ሁሉ ለእነርሱም “አልታዘዛችሁኝም። ለምን ይህንን አደረጋችሁ?” ይላቸዋል:: The Signs of the Times, June 2, 1881. MYPAmh 274.2