Go to full page →

እውነተኛ ፍቅር MYPAmh 276

ፍቅር ከየሱስ የምንቀበለው ውድ ሥጦታ ነው። ንፁህና ቅዱስ ፍቅር ስሜት ሳይሆን መርህ ነው። በእውነተኛ ፍቅር የተነሣሱ ሰዎች ጭፍኖችና ምክንያት የለሾች አይደሉም። ከመንፈስ ቅዱስ የተማሩ ስለሆነ እግዚአብሔርን ከሁሉም በላይና ጎረቤታቸውን እንደራሳቸው ይወዳሉ። MYPAmh 276.1

ስለ ጋብቻ በማሰላሰል ላይ ያሉ ሁሉ ወደ ፊት በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አብረው ለመኖር ስለሚያስቡት ሰው እያንዳንዱን አመለካከት ማመዛዘንና እያንዳንዱን የፀባይ እድገት በጥንቃቄ መመልከት አለባቸው። እያንዳንዱ ለጋብቻ ህብረት የሚወሰድ እርምጃ በጨዋነት፣ በትህትና፣ በእውነተኛነት፣ እግዚአብሔርን ለማስደሰትና ለማስከበር ካለ ጥልቅ ፍላጎት ይሁን። ጋብቻ የወደፊት ህይወትን በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ዓለም ይነካል። እውነተኛ ክርስቲያን እግዚአብሔር የማይደግፈውን ማንኛውንም እቅድ አያቅድም። MYPAmh 276.2