Go to full page →

ጓደኞችን መምረጥ MYPAmh 276

ጓደኝነትን በመፍጠርና ወዳጆችን በመምረጥ ረገድ በክርስቲያን ወጣቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ተጠንቀቅ! ዛሬ ንፁህ ወርቅ ነው ብለህ የምትገምተው ነገር ነጌ ተራ ብረት ሊሆን ይችላል። ዓለማዊ ህብረቶች ለእግዚአብሔር በምታደርገው አገልግሎት ላይ እንቅፋት ሊሆኑብህ ይችላሉ። ከእነዚህ ዓይነት ፀባያቸውን ለማነፅ ከማይረዱ ጓደኞች ጋር ያልሆኑ ህብረቶችን በስራም ሆነ በጋብቻ በመፍጠር ብዙ ነፍሳት ጠፍተዋል። የእግዚአብሔር ህዝቦች በተከለከለ ህብረት ውስጥ በፍፁም መግባት የለባቸውም። በሚያምኑና በማያምኑ መካከል የሚደረግ ጋብቻ በእግዚአብሔር የተከለከለ ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ያልተለወጠ ልብ የራሱን ፍላጎት ስለሚከተል በእግዚአብሔር ያልተፈቀዱ ጋብቻዎች ይፈፀማሉ። Fundamentals of Christian Education P. 500. MYPAmh 276.6