Go to full page →

በኃይማኖት ልምምድ ተጽእኖ ማሳደር MYPAmh 277

በስድ ፍቅር ተይዘህ የእግዚአብሔር ፍቅር ከሌላትና መንፈሳዊ ሕይወት ስሜት ከማይሰጣት ሴት ጋር አብረህ ለመደሰት በተደጋጋሚ ከፀሎት ስብሰባዎች የምትቀር ከሆንክ የዚህን ዓይነቱን አንድነት እግዚአብሔር ይባርከዋል ብለህ እንዴት ትጠብቃለህ? MYPAmh 277.3

አትቸኩል። ያለጊዜ ጋብቻዎች መደፋፈር የለባቸውም። ወንድ ወጣቶችም ሆኑ ሴት ወጣቶች ከኃይማኖት ጋር ለሚያስተሳስራቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ አክብሮት ከሌላቸው ከአንድ ባልም ሆነ ሚስት የሚጠበቀውን ሃላፊነት የመወጣት አደጋ አለባቸው። መንፈሳዊ እድሎችንና የፀሎት ሰዓቶችህን መስዋዕት በማድረግ ከምትወደው ሰው ጋር ሁልጊዜ አብሮ ለመሆን የመፈልግ ልምድ አደገኛ ነው። ልታካክሰው የማትችል ክስረት ውስጥ ትገባለህ። MYPAmh 277.4

ምንም እንኳን ሁለታችሁም ክርስቲያን ብትሆኑም በምሽት እስከ ረፋድ ድረስ መቀመጥ ለእግዚአብሔር አያስደስተውም። እነዚህ መዘግየቶች ጤናን የማጓደል፣ አእምሮን ለቀጣዩ ቀን ሥራ ገጣሚ እንዳይሆን የማድረግና የክፋት ስሜት ይፈጥራሉ። ወንድሜ ሆይ! የዚህን ዓይነት ግንኙነት እምቢ ማለት የሚያስችልህ ራስህን የማክበር ችሎታ እንዳለህ ተስፋ አደርጋለሁ። ለእግዚአብሔር የቆመ ዓይን ካለህ ማስጠንቀቂያውን እያየህ ትሄዳለህ። እንደ ክርስቲያን እግዚአብሔር በአንተ ላይ ያለውን ዓላማ መለየት እስከማትችልና አመለካከትህ እስኪጨልም ድረስ ለፍቅር ህመምተኝነት ስሜት ራስህን አታስገዛም። Testimonies for the Church, V.3, P. 44-45. MYPAmh 277.5