Go to full page →

ፍፁም መሪ MYPAmh 281

መጽሐፍ ቅዱስ የባሕርይን ፍፁም መስፈርት ያስቀምጥልናል። ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትና ቅዱሳን ሰዎች የፃፉት ቅዱስ መጽሐፍ በህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ ሁሉ ፍጹም የሆነ መሪ ነው። የወጣቶችንም ሆነ የአዛውንቶችን ሃላፊነቶች በግልጽ ያስቀምጣል። የሕይወት መሪ ተደርጎ ቢወሰድ አሰተምሮው ነፍስን ወደ ላይ ይመራል። አእምሮን ከፍ ያደርጋል፣ ባሕርይን ያሻሽላል፣ ለልብም ሰላምና ደስታ ይሰጣል። ነገር ግን ብዙ ወጣቶች የራሳቸው መሪና አማካሪ መሆንን መርጠዋል! ከዚህም የተነሣ ጉዳያቸውን በራሳቸው እጅ ይዘውታል። እንደ እነዚህ ዓይነት ወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት የበለጠ በቅርበት ማጥናት ያስፈልጋቸዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ገፆች ላይ ለወላጆቻቸውና በእምነት ወንድሞቻቸው ለሆኑት ያለባቸውን ሃላፊነት ተገልጦ ያገኙታል:: አምስተኛው ትእዛዝ “እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር እድሜህ ይረዝም ዘንድ አባትህንና እናትህን አክብር፡፡” ይላል:: እንደገና “ልጆች ሆይ፣ ይህ በጌታ ትክክል ስለሆነ ለወላጆቹችሁ ታዘዙ::” የሚለውን እናነባለን። MYPAmh 281.3

እኛ በመጨረሻ ዘመን እየኖርን ለመሆናችን ከተሰጡት ምልክቶች አንዱ ልጆች ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው መሆናቸውን ነው። የእግዚአብሔር ቃል ወላጆችን ማክበር እንዳለብን በሚገልፁ ጥቅሶችና ምክሮች የተሞላ ነው። በወጣቶች አእምሮ ከህፃንነት ጀምሮ በልጅነት እድሜ፣ በወጣትነት እድሜና እስከ ሙሉ ወንድና ሴት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ የሚመሯቸውንና የተጠነቀቁላቸውን፣ አሁን ግን ሰላምና ደስታን ለማግኘት በከፍተኛ ደረጃ በልጆቻቸው ላይ የሚደገፉትን ወላጆች የማፍቀርና የመጠንቀቅ ቅዱስ ሃላፊነት በአእምሮ ውስጥ ያሰርፃል። መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ ላይ አጠራጣሪ የሆነ ድምፅ አያሰማም! ሆኖም ይህ አስተምሮ በከፍተኛ ደረጃ ችላ ተብሏል። MYPAmh 281.4

ወጣቶች መማር ያለባቸው ብዙ ትምህርቶች አሉ:: ከእነዚህ ትምህርቶች እጅግ አስፈላጊው ራሳቸውን ማወቅን መማር ነው። ለወላጆቻቸው ስላላቸው ግዴታዎችና ሀላፊነቶች ትክክለኛ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። በልባቸው ትሁትና የዋህ ለመሆን በክርስቶስ ትምህርት ቤት ያለማቋረጥ መማር አለባቸው። ወላጆቻቸውን እየወደዱና እያከበሩ ሳለ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ልምድ ያላቸው ሰዎችን ውሳኔም ማክበር አለባቸው። MYPAmh 282.1