Go to full page →

የምክርና አቅጣጫ የማሰየት አስፈላጊነት MYPAmh 281

በእነዚህ አደጋና ክፋት በሞላባቸው ቀናት ወጣቶቻችን ለብዙ ችግሮችና ፈተናዎች የተጋለጡ ናቸው። ብዙዎች አደገኛ በሆነ ወደብ ላይ እየቀዘፉ ናቸው። የመርከቡን መግባትና መውጣት የሚቆጣጠር ሰው ያስፈልጋቸዋል! ነገር ግን የራሳቸውን መርከብ ለመምራት በራሳቸው ብቁ እንደሆኑ እየተሰማቸው የእምነታቸውንና የደስታቸውን መርከብ ሊሰባብር ከሚችል የተደበቀ አለት ጋር ሊጋጩ እንደሆኑ ሳይገነዘቡ እጅግ በሚያስፈልጋቸው እርዳታ ላይ እያሾፉ ናቸው። ከጋብቻ በፊት በሚኖር መቀራረብና በጋብቻ እጅግ ስለተመሰጡ ዋና ሸክማቸው የራሳቸውን መንገድ መከተል ነው። በዚህ ከህይወታቸው እጅግ አስፈላጊ በሆነው ወቅት የማይሳሳት አማካሪና መሪ ያስፈልጋቸዋል። ይህንን ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያገኙታል። የዚህ ቃል ትጉህ ተማሪዎች ካልሆኑ በስተቀር በአሁኑም ሆነ በወደፊት ሕይወት የራሳቸውንም ሆነ የሌሎችን ደስታ ሊያበላሹ የሚችሉ አሰቃቂ ስህተቶችን ይፈጽማሉ። MYPAmh 281.1

በብዙዎች ዘንድ የችኩልነትና በራሳቸው አእምሮ ብቻ የመመራት ሁኔታ ይታያል። የእግዚአብሔርን ቃል የጥበብ ምክር አልሰሙም! ከራሳቸው ጋር ጦርነት ገጥመው የከበረ ድል አላገኙም። የራሳቸው ኩሩና የማይታጠፍ ፈቃዳቸው ከተግባርና ከመታዘዝ መንገድ አርቋቸዋል። ወጣት ወዳጆች ሆይ፣ያለፈውን ሕይወታችሁን ወደ ኋላ ተመልከቱና የሄዳችሁበትን መንገድ በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን እዩት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለወላጆቻችሁ ያለባችሁን ግዴታዎች የሚገልፀውን አስተውላችሁ ፈፅማችሁታልን? ከህፃንነታችሁ ጀምራ የተጠነቀቀችላችሁን እናታችሁን በደግነትና በፍቅር ይዛችኋታልን? የእርሷን ምኞት ፈጽማችሁላታልን? ወይስ የራሳችሁን ፍላጎትና እቅድ በመፈፀም ልቧን በሐዘንና በሥቃይ ሞልታችሁታል? ያመናችሁት እምነት ልባችሁን ቀድሶ ፈቃዳችሁን ልስልስና ታዘዥ አድርጎታልን? ይህ ካልሆነ ያለፈውን ሥህተታችሁን ለማረም በቅርበት የምትሰሩት ሥራ አለ። MYPAmh 281.2