Go to full page →

የድል መንሳት ዋጋ MYPAmh 43

በክፉና በመልካም መካከል ያለው ጦርነት አዳኙ በምድር ላይ ከኖረበት ጊዜ ይልቅ አሁን ጥንካሬው አልቀነሰም፡፡ የሰማይ መንገድም ያኔ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ የተስተካከለ አይደለም፡፡ ኃጢአቶቻችን በሙሉ መወገድ አለባቸው፡፡ መንፈሳዊ እድገትን የሚከለክል እያንዳንዱ ማራኪ ፍላጎት ከሕይወታችን መቆረጥ አለበት:: የሚያሰናክለን ከሆነ የቀኝ እጃችን ወይም የቀኝ ዓይናችን መሰዋት አለበት:: የራሳችንን ጥበብ ትተን የእግዚአብሔርን መንግስት እንደ ትንሽ ህጻን ለመቀበል ፈቃደኛ ነን ወይ? ከራስ ፅድቃችን ለመለየት ፈቃደኛ ነን ወይ? የሰዎችን ድጋፍ መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ ነን ወይ? የዘላለም ህይወት ሽልማት ገደብ የለሽ ዋጋ ያለው ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ለመቀበል፣ አብሮ ለመሥራት፣ ጥረት ለማድረግና ወደፊት ልናገኘው ከምንጠብቀው ዋጋ ጋር የሚመጣጠን መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ ነን ወይ? Review and Herald, Feb 10, 1903. MYPAmh 43.1