Go to full page →

ቀደምት ተያያዥነት ያለው አደጋ MYPAmh 286

በልጅነት እድሜ የሚፈጠሩ ግንኙነቶች ያላቸው አደጋ የልጅነት ጥምረት በጣም አሳዛኝ የሆነ አንድነትን ወይም አስቀያሚ መለያየትን ፈጥሮአል። ወላጅን ሳያማክሩ የተፈጠሩ የልጅነት ጋብቻዎች አብዛኛዎቹ ደስታ የሌለባቸው ናቸው። የልጅነትን ፍቅር በቂ እድሜና ልምድ የከበረ እስኪያደርገው ድረስ መገታት አለበት። መገታትን የማይፈልጉ ደስታ በሌለበት ሕይወት ውስጥ የመግባት አደጋ ውስጥ ይሆናሉ። የጉርምስና እድሜን ያላለፈ ወጣት ልክ እንደ ራሱ ያለ ወጣት ሰው የህይወት ጓደኛ ለመሆን ገጣሚ መሆን አለመሆኑን ለመወሰን አይችልም። አእምሮአቸው ሲበስል እርስ በርሳቸውን ደስተኛ ለማድረግ የማይችሉ ሰዎች ለሕይወት ዘመን አንድነት መጣመራቸውን ይመለከታሉ። ከዚያ በኋላ ካጋጠማቸው ዕጣ ውስጥ የተሻለውን ለማግኘት ከመሞከር ይልቅ ለእርስ በርሳቸው ግድ የለሾችና ቸልተኞች ይሆኑና መወነጃጀል ይጀምራሉ፣ ልዩነትም እየሠፋ ይሄዳል። ለእነርሱ ቤት በሚለው ቃል ውስጥ ምንም የተቀደሰ ነገር አይኖርም። የቤት ከባቢ አየር ፍቅር በሌላቸው ቃላትና መራር በሆኑ ነቀፌታዎች ይመረዛል። A Solemn Appeal, P.11-12. (Edition: Signs Publishing Company Limited). MYPAmh 286.2