Go to full page →

በጥበብና ያለ ጥበብ የተፈፀሙ ጋብቻዎች MYPAmh 287

ብስለት የሌላቸው ጋብቻዎች ዛሬ ላሉ ብዙ ክፉ ነገሮች ምክንያት ናቸው። በልጅነት የተገባበት ጋብቻ የአካል ጤንነትንም ሆነ የአእምሮ ብርታትን አይጨምርም። ለዚህ ጉዳይ በጣም ጥቂት ግምት ተሰጥቶታል። ብዙ ወጣቶች ጋብቻን በስሜት ይፈጽማሉ። ይህ ለመልካም ወይም ለመጥፎ፣ ለህይወት ዘመን በረከት ወይም መርገም የሚያበቃ እርምጃ በጥድፊያና በስሜት በመገፋፋት ይወሰዳል። ብዙዎች ከክርስቲያናዊ አመለካከት የሚመጡ ምክንያቶችንም ሆነ መመሪያዎችን አይቀበሉም። MYPAmh 287.1

በስህተት በተቀናጁ ጋብቻዎች ምክንያት ዛሬ ዓላማችን በሐዘንና በኃጢአት ተሞልቶአል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ባልና ሚስት በፍፁም የማይጣጣሙ መሆናቸውን ለማወቅ ጥቂት ወራት ብቻ ይፈጃል። ውጤቱም የሰማይ ፍቅርና ስምምነት መኖር በነበረበት ቤት አለመስማማት መፈጠር ነው። MYPAmh 287.2

ጥቃቅን በሆኑ ነገሮች ካለመስማማት የተነሣ መራራ መንፈስ ይዘራል። ግልፅ የሆኑ አለመስማማቶችና ጭቅጭቆች ሊገለፅ የማይቻል ስቃይ በማምጣት በፍቅር ሰንሰለት መያያዝ ያለባቸውን ይለያዩአቸዋል። በመሆኑም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ማስተዋል ባነሰው ጋብቻ ምክንያት ራሳቸውን፣ ነፍሳቸውንና አካላቸውን በመሰዋት በጥፋት መንገድ ሄደዋል። MYPAmh 287.3