Go to full page →

ማግባትና መጋባት MYPAmh 289

እግዚአብሔር ሰዎችን በዚህች ዓለም ላይ አስቀምጧቸዋል። ስለዚህ መብላትና መጠጣት፣ ማግባትና መጋባት መብታቸው ነው። ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ደህንነትን የሚያመጡት በፈሪሃ እግዚአብሔር ሲፈፀሙ ብቻ ነው። በዚህ ዓለም መኖር ያለብን ከዘላለማዊው ዓለም ጋር ባለን ግንኙነት ነው። የኖህ ዘመን ታላቁ የጋብቻ ወንጀል የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ልጆች ማግባት ነበረ። እግዚአብሔርን እናከብራለን ይሉ የነበሩ ሰዎች ልባቸው ከረከሰ ህዝብ ጋር ህብረት ፈጠሩ። ያለ አንዳች ልዩነት የወደዱትን ሁሉ አገቡ። በዛሬም ጊዜ የኃይማኖት ልምምድ ጥልቀት የሌላቸው ሰዎች የኖህ ዘመን ሰዎች ያደረጉትን ያንኑ ተግባር ይፈጽማሉ። ብዙዎች ይህንን ቅዱስ ቃል ኪዳን እንደ ንግድ ልውውጥ ያለ ሀሳብ ይገቡበታል። ለህብረታቸው ምክንያቱ እውነተኛ ፍቅር አይደለም። MYPAmh 289.1