Go to full page →

በራስ መተማመን አደገኛ ነው MYPAmh 44

ሰይጣን ሰብዓዊ አእምሮን በማታለል ሟቾች በውስጣቸው በውርስ ያገኙት ታላላቅና መልካም ሥራዎችን የመፈፀም ኃይል እንዳለ እንዲያምኑ ማድረግ ቢችል ኖሮ በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን ይተውና በውስጣቸው ለማድረግ የሚያስችል ኃይል እንዳለ ወደ ሚያስቡት መደገፍ ይጀምራሉ፡፡ ከእነርሱ በላይ የሆነ ኃይል መኖሩን አይቀበሉም፡፡ ለእግዚአብሔር ታላቅና ግሩም ለሆነው ንጉሥነቱ የሚገባውን ክብር አይሰጡም፡፡ ያኔ የሰይጣን ዓላማው ተፈፀመ ማለት ነው፡፡ ሰይጣን በሰማይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግ ወደ ምድር እንደተጣለ ሁሉ የወደቀው ሰብዓዊ ዘርም ራሱን ከፍ ከፍ በማድረጉ ሰይጣን ይደሰታል፡፡ ሰው ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ከሆነ ሰይጣን አስቀድሞ ይህንን በማድረጉ ጥፋቱ እርግጠኛ እንደ ሆነ ሁሉ የሰው ጥፋትም እርግጠኛ እንደሚሆን ያውቃል፡፡ MYPAmh 44.5