Go to full page →

መተማመንን ማጥፋት MYPAmh 44

ሰይጣን በምድረ በዳ ፈተና አልተሳካለትም:: የድነት እቅድ ተከናውኖአል፡፡ ለሰው ድነት ውድ ዋጋ ተከፍሏል፡፡ አሁን ሰይጣን የሚሻው የክርስቲያኖችን ተስፋ መሰረት ለመናድና የሰዎችን አእምሮ በተደረገው ታላቅ መስዋዕትነት እንዳልዳኑ ወይም ምንም ጥቅም እንዳላገኙበት ወደ ሚገልጽ መስመር መቀየር ነው፡፡ የወደቀውን ሰው በማታለያውና በእርኩሰቱ ሁሉ ያለ አንዳች ሥርየት የተከናወነ ሕይወት መኖር እንደሚቻል እንዲያምን ይመራዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ በተሰቀለውና ከሙታን በተነሳው መታመን አስፈላጊ አለመሆኑን ይገልፃል፡፡ የሰው የራሱ መልካም ሥራ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲያገኝ ያስችለዋል በማለት ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያላቸውን እምነት ያፈጣል፡፡ በዚህ ከተሳካለት ስህተቱን የሚያሳይ መጠቆሚያ መሳሪያ ስለሚጠፋ እርሱ ከአደጋ ነፃ እንደሚሆን ያምናል፡፡ MYPAmh 44.6

በአካል የሚገለጽ ሰይጣን የሚባል ነገር የለም የሚለውን ማታለያ በሰዎች አእምሮ ውስጥ ያስገባል፡፡ ይህንን የሚያምኑ ደግሞ ከሌለ ጠላት ጋር ለመዋጋትና ለመቋቋም ምንም ጥረት አያደርጉም፡፡ በመሆኑም እነዚህ ምስኪንና የታወሩ ሟቾች በመጨረሻ «ምንም ቢሆን ትክክል ነው» የሚለውን ፈሊጥ እንዲቀበሉ ያደርጋል፡፡ የድርጊታቸው መለኪያ የሚሆንን ምንም ደንብ አይቀበሉም፡፡ ሰይጣን ብዙዎችን ፀሎት ዝም ብሎ የይስሙላ እንጂ ዋጋ እንደ ሌለው እንዲያምኑ ይመራቸዋል፡፡ ፀሎትና የማሰላሰል ጊዜ ክርስቲያኖች ነቅተው በመጠበቅ የሰይጣንን ተንኮልና ማታለያ ለመቋቋም ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በደንብ ያውቃል፡፡ የሰይጣን የተለያዩ ወጥመዶች አእምሮን ከእነዚህ ጠቃሚ ልምምዶች ይመልሱና ነፍስ ለእርዳታ ብርቱ በሆነው ላይ እንዳትደገፍና ጥቃቶችን ለመከላከል ብርታት ከጌታ እንዳታገኝ ያደርጋል፡፡ MYPAmh 45.1

የፀሎት ልምምዳችንን ቸል ማለት የጠላትን የውሸት ተአምራቶች በቀላሉ እንድንቀበል በማድረግ የራሱን ዓላማ በደንብ ያገለግላል፡፡ ሰይጣን ዓላማውን የሚፈጽመው በሰዎች ፊት አታላይ ፈተናዎችን በማስቀመጥ ነው፡፡ ይህን ዘዴ በመጠቀም ኢየሱስን ለመፈተን የሞከረ ቢሆንም አልተሳካለትም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወደ እኛ የሚመጣው በሚያምር ሰው ወይም በሚያምር ጥላ ነው፡፡ የፈውስ ሥራዎችን በመስራት በተታለሉ ሟቾች ዘንድ የእኛ ትውልድ ሥጦታ ሰጭ ተደርጎ ይመለካል፡፡ MYPAmh 45.2