Go to full page →

በጌታ ብርታት MYPAmh 48

ኢየሱስ የዓለም ብርሃን ስለሆነ እናንተም ሕይወታችሁን በእርሱ አምሳያ ማስተካከል አለባችሁ፡፡ ጠንካራ፣ የተስተካከለና ያማረ ባሕርይ ለመመስረት እርዳታን ከኢየሱስ ታገኛላችሁ፡፡ ከእንደዚህ ዓይነት ባሕርይ የሚፈነጥቀውን ብርሃን ሰይጣን ውጤተ ቢስ ማድረግ አይችልም፡፡ ጌታ ለእያንዳንዳችን ሥራ አለው፡፡ ያንን ሥራ የሚሰጠን በሰዎች ሙገሳና ቁልምጫ ተጽዕኖ ሥር እንድንሆን አይደለም፡፡ እርሱ ሊለን የሚፈልገው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ ነፍስ በጌታ ብርታት መቆም ይችላል ነው፡፡ የራሱን የባሕርይ ፍጽምና በእኛ ላይ በማድረግ በመንግስቱ ላለው ቤት ገጣሚዎች እንድንሆን ከፍ ሊያደርገንና ሊያከብረን ከሁሉ የተሻለውን ሥጦታ ያውም አንድያ ልጁን ሰጥቶናል፡፡ ኢየሱስ ወደ እኛ ዓለም መጥቶ ተከታዮቹ እንዲኖሩ የሚጠብቅባቸውን ዓይነት ሕይወት ኖረ፡፡ በራስ ደስታ የተያዝንና ከእግዚአብሔር አስደናቂ ሥራ ጋር ለመተባበር ልባዊ ጥረት እንዳናደርግ ሰነፎች ከሆንን በዚህኛውም ሆነ በሚመጣው ዘላለማዊ ሕይወት ኪሳራ ይገጥመናል፡፡ MYPAmh 48.3

እግዚአብሔር ሥራውን እንድንሰራ ያቀደው ተስፋ በመቁረጥ ሳይሆን በጠንካራ እምነትና ተስፋ ነው፡፡ ቃሉን ስናጠና፣ የሰማይ አባት ልጁን ኢየሱስን ለዚህ ዓለም በመስጠት ያደረገውን አስደናቂ ደግነት ለማየት ብርሃን ስናገኝና በእርሱ ያመነ ሁሉ እንደማይጠፋ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኝ ስንረዳ፣ ሊነገር በማይቻልና በግርማ በተሞላ ደስታ ደስ ሊለን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር የሚለው እያንዳንዱን በትምህርት ያገኘነውን ነገር እውነትን ለማስፋፋት መጠቀም እንደምንችል ነው፡፡ የክርስቶስ መስቀል በዓለም ፊት ከፍ እንዲልና በመስቀል ብርሃን የነፍስ ዋጋ እንዲገለጥ እውነተኛው አምልኮ በሕይወትና በባሕርይ ውስጥ መንፀባረቅ አለበት፡፡ የሰማይን እንጀራ በመመገብ መንፈሳዊ ኃይል ማግኘት እንድንችል አእምሮቻችን ለቃሉ ማስተዋል መከፈት አለባቸው፡፡ Review and Herald, April 8,1990. MYPAmh 48.4