Go to full page →

የነፍስ ቤተመቅደስ MYPAmh 49

እግዚአብሔር ለሰጠን መስፈርቶች ታማኝነት ያለበት መታዘዝ የሰውን የተፈጥሮ ኃይሎች ከፍ ለማድረግ፣ ለማጎልበትና ለማጽናት አስገራሚ ተጽእኖ አለው፡፡ በወጣትነታቸው እግዚአብሔርን ለማገልገል ራሳቸውን የለዩ ሰዎች ሚዛናዊ የአእምሮ ግንዛቤ ያላቸው፣ ነገሮችን በትክክል መለየት የሚችሉ ሰዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ዓለም እስከ አሁን ካወቃቸው መምህራን ሁሉ ታላቁ መምህር ከሆነው መምህር ጋር ግንኙነት መፍጠር ማስተዋልን ያጠነክራል፣ አእምሮን ያበራል፣ ልብን ያነጻል፣ ሰውየውን በሞላ ከፍ ያደርገዋል፣ ያጠራዋል፣ እንዲሁም የከበረ ያደርገዋል፡፡ «የቃልህ መግቢያ ብርሃን ይሰጣል፤ ለትሁቱ ሰው ማስተዋልን ይሰጠዋል፡፡» MYPAmh 49.1