Go to full page →

ኃይሎቻችን በሙሉ የእርሱ ናቸው MYPAmh 51

የእግዚአብሔር ማህተም በላያችን ነው፡፡ እርሱ ገዝቶናል፤ በመሆኑም የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ኃይሎቻችን የእርሱ መሆናቸውን እንድናስታውስ ይፈልጋል፡፡ ጊዜና ተጽእኖ፣ አስተሳሰብ፣ ፍቅርና ህሊናችን በሙሉ የእግዚአብሔር ስለሆኑ ከእርሱ ፈቃድ ጋር በተጣጣመ መልኩ ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው፡፡ ዓለም በሚመራን መስመር ጥቅም ላይ መዋል የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም ዓለም የእግዚአብሔር ጠላት በሆነው መሪ ሥር ነች፡፡ MYPAmh 51.6

ነፍስ መቅደስዋን ያደረገችበት ሥጋችን የእግዚአብሔር ነው፡፡ እያንዳንዱ ጅማትና ጡንቻ የእርሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ በምንም ምክንያት በቸልተኝነትም ይሁን ያለ አግባብ በመጠቀም የአካል ክፍሎቻችንን ማዳከም የለብንም፡፡ አካላችንን በተቻለን መጠን ልናቆየው በምንችለው ጤናማ ሁኔታ ለመቆየት ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር አለብን፡፡ ያኔ መንፈስ ቅዱስ የሚያድርበት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ይሆናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን አካላዊና መንፈሳዊ ኃይል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይቀርጸዋል፡፡ MYPAmh 51.7

አእምሮአችን የንፁህ መርሆዎች መከማቻ መሆን አለበት፡፡ እውነት በነፍስ ፅላቶች ላይ መቀረፅ አለበት፡፡ የአእምሮአችን የሚያስታውሰው ክፍል በቃሉ ውድ እውነቶች መሞላት አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ እንደሚያምሩ እንቁዎች እነዚህ እውነቶች በሕይወት ውስጥ ያብረቀርቃሉ፡፡ MYPAmh 51.8