Go to full page →

የነፍስ ዋጋ MYPAmh 52

እግዚአብሔር ለእጁ ሥራዎች የሚሰጠው ዋጋ፣ እርሱ ለልጆቹ ያለው ፍቅር፤ የተገለፀው ሰዎችን ለማዳን በሰጠው ሥጦታ ነው፡፡ አዳም በሰይጣን ግዛት ሥር ወደቀ፡፡ ወደ ዓለም ኃጢአትን አመጣ፤ በኃጢአትም ሞትን አመጣ፡፡ ሰውን ለማዳን እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ሰጠ:: ይህን ያደረገው ጻድቅ ለመሆንና የሱስን የሚቀበሉትን የሚያፀድቅ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ሰው ራሱን ለሰይጣን ሸጠ፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሰብዓዊ ዘርን መልሶ ገዛ፡፡ MYPAmh 52.1

እናንተ የራሳችሁ አይደላችሁም ፡፡ የሱስ በራሱ ደም ገዝቶአችኋል፡፡ መክሊቶቻችሁን በአፈር ውስጥ አትቅበሩ፡፡ ለእርሱ ሥራ ተጠቀሙባቸው፡፡ በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ብትሰማሩ የሱስን ወደ ሥራችሁ አምጡት፡፡ ለአዳኛችሁ ያላችሁን ፍቅር በሥራችሁ ምክንያት እያጣችሁ ከሆነ ሥራችሁን ተውና እንዲህ በሉ፡- «አዳኝ ሆይ እዚህ አለሁ፡፡ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋልህ?” እርሱ በፀጋው ይቀበለንና በነፃ ይወደናል፡፡ እርሱ ይቅር ባይ፣ ታጋሽና ማንም እንዲጠፋ የማይፈቅድ ስለሆነ በነፃ ይቅር ይለናል፡፡ MYPAmh 52.2

እኛና ያለን ነገር ሁሉ የጌታ ነው፡፡ የልብ ፍቅራችንን ለርሱ ስንሰጥ እንደ መስዋዕት አድርገን አንየው፡፡ ልብ እራሱ እንደፈቃድ ስጦታ ለእርሱ ሊሰጥ ይገባል፡፡ —The Youth’s Instructor, November 8, 1900. MYPAmh 52.3