Go to full page →

ስሜት ሳይሆን የተለወጠ ሕይወት MYPAmh 53

ሰይጣን ሰዎችን በስሜታቸው ደስተኛ ከሆኑ ተለውጠናል ብለው እንዲያስቡ ይመራቸዋል፡፡ ነገር ግንየሕይወት ልምዳቸው አይለወጥም፡፡ ድርጊታቸው ከድሮዎቹ ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሕይወታቸው ጥሩ ፍሬ አያሳይም፡፡ ቶሎ ቶሎ ይፀልያሉ፤ ይናፍቃሉም፡፡ በእነዚህ ሰዓታት የሚያነቡት ከዚህ በፊት በዚህና በዚህ ሰዓት የተሰማቸውን ስሜት ነው፡፡ ነገር ግን አዲስ ህይወት አይኖሩም:: ተታለዋል፡፡ ልምምዳቸው ከስሜት ያለፈ ጥልቀት የለውም፡፡ በአሸዋ ላይ ስለሚገነቡ አደገኛ ንፋስ በመጣ ጊዜ ቤታቸው ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡ MYPAmh 53.3

ብዙ ምስኪን ነፍሳት ከዚህ በፊት በሕይወት ልምምዳቸው ውስጥ ሌሎች ነበሩአችሁ ያሉአቸውን ስሜቶች በመፈለግ በጨለማ ውስጥ እየዳከሩ ናቸው፡፡ በክርስቶስ የሚያምን መዳኑን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ መሥራት እንዳለበት የሚገልፀውን እውነት ችላ ይላሉ፡፡ የተፈረደበት ኃጢአተኛ ማድረግ ያለበት ነገር አለ፡፡ መናዘዝና እውነተኛ እምነት ማሳየት አለበት፡፡ MYPAmh 53.4

ኢየሱስ ስለ አዲስ ልብ ሲናገር ስለ አእምሮ፣ ስለ ሕይወትና ስለ ሁለመናችን መናገሩ ነው፡፡ የልብ ለውጥ ማግኘት ማለት ለዓለም ያለንን ፍቅር መተውና በኢየሱስ ላይ ማተኮር ማለት ነው፡፡ አዲስ ልብ ማግኘት ማለት አዲስ አእምሮ፣ አዲስ ዓላማዎች፣አዲስ የሥራ ተነሳሽነት ማግኘት ማለት ነው፡፡ የአዲስ ልብ ምልክቱ ምንድን ነው? የተለወጠ ሕይወት ነው፡፡ በየቀኑና በየሰዓቱ ለራስ ወዳድነትና ለትዕቢት መሞት ማለት ነው፡፡ MYPAmh 53.5