Go to full page →

እውነተኛ መለወጥ MYPAmh 53

«የጠራ ውኃ እረጭባችኋለሁ እናንተም ትነፃላችሁ፡፡ ከእርኩሰታችሁ ከጣዖቶቻችሁ አነፃችኋለሁ፡፡ አዲስ ልብ እስጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስም በውስጣቸሁ አኖራለሁ፡፡ የድንጋይን ልብ ከውስጣችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ፡፡. MYPAmh 53.1

ብዙዎች ለሌሎች አዲስ ልብ እንደሚያስፈልግ የሚናገሩ ራሳቸው እነዚህ ቃላት ምን ማለታቸው እንደሆነ አያውቁም፡፡ በተለይ ወጣቶች በዚህ «አዲስ ልብ» በሚለው ሃረግ ላይ ይደናቀፋሉ፡፡ ምን ማለት እንደሆነ አያውቁም፡፡ የተለየ ለውጥ በስሜታቸው ውስጥ እንዲሆን ይሻሉ፡፡ ይህንን እነርሱ መለወጥ ይሉታል፡፡ «እንደገና መወለድ አለባችሁ” የሚለውን መግለጫ ካለማስተዋል የተነሳ በዚህ ስህተት ላይ በሺሆች የሚቆጠሩ ተደናቅፈዋል፡፡ MYPAmh 53.2