Go to full page →

የኃጢአት አታላይነት MYPAmh 60

ከኃጢአት አታላይነት የበለጠ አሳች ነገር የለም፡፡ የሚያታልለው፣ የሚያሳውርና ወደ ጥፋት የሚመራው የዚህ ዓለም አምላክ ነው፡፡ ሰይጣን የማታለያ ዝግጅቶቹን ይዞ በአንዴ አይመጣም፡፡ ፈተናዎቹን በሚያምር ቀለም ይሸፍናቸዋል፡፡ ከሥጋዊ ደስታ ፍላጎትና ከንቱነት ጋር ጥቂት ከዚህ ግባ የማይባሉ መሻሻሎችን ይቀላቅልና የተታለሉ ነፍሶች በእነዚህ ነገሮች በመሳተፍ ታላቅ መልካም ነገር ይገኝበታል የሚል ሰበብ እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡ ይህ አሳሳቹ ክፍል ነው፡፡ የሰይጣን ገሃነማዊ ጥበባት የተሸፈኑበት ዘዴ ነው፡፡ የተታለሉት ነፍሳት አንድ እርምጃ ከሄዱ ለሁለተኛው እርምጃ ታዘጋጅተዋል ማለት ነው፡፡ የተንኮለኛ ጠላትን የመጀመሪያ ማታለያዎችን ከመቋቋም፣ ከመከላከልና ከእርሱ ለሚመጡ ነገሮች ሁሉ ራስን ዝቅ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸውን የልብ ዝንባሌ መከተል እጅግ ይቀላቸዋል፡፡ MYPAmh 60.1

ሰይጣን ማታለያዎቹ በቀላሉ ተቀባይነት ሲያገኙና ነፍሳት እርሱ ባዘጋጀው መንገድ ሲጓዙ ለማየት ምንኛ በንቃት ይጠብቃል! ፀሎትን እንዲያቆሙና፣ ውጫዊ የኃይማኖት መልክ እንዳይኖራቸው አይፈልግም፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ በራሱ አገልግሎት የበለጠ ጠቃሚ ስለሚሆኑት ነው፡፡ የማታለያ የውሸት መከራከሪያዎችንና አታላይ ወጥመዶቹን ከእነርሱ ልምምድና እምነት ጋር በማዋሃድ ዓለማውያን በአስደናቂ ሁኔታ ወደ ፊት እንዲቀጥሉለት ያደርጋል፡፡ MYPAmh 60.2