Go to full page →

ከዝንባሌ ያለፈ ተግባር (ሃላፊነት) MYPAmh 59

ወጣቶች ከሰይጣን ቁጥጥር ሥር ለማምለጥ ሲሞክሩ ሰይጣን ፈተናዎቹን እጥፍ ያደርጋል፡፡ አለማወቃቸውንና የልምድ ማነሳቸውን አጋጣሚ በመጠቀም በክፉና በመልካም መካከል ያለውን ልዩነት ሊደብቅባቸው ይሞክራል፡፡ ራሱን በብርሃን መልአክ በማስመሰልና በተከለከለ መንገድ የሚገኝ የደስታ ተስፋ በመስጠት ያታልላል፡፡ ወጣቶች ከተግባር ይልቅ ዝንባሌን የመከተል ልምድ አዳብረው ከሆነ ፈተናን መቋቋም ይከብዳቸዋል፡፡ አንድ ጊዜ እንኳን በተከለከሉ ደስታን የማግኛ ዘዴዎች መሳተፍ ያለውን አደጋ አያዩም፡፡ የሰይጣን አስተያየቶች እያንዳንዱን በውስጥ ያሉ ክፋቶችን ወይም የሞራል ብልሽትን ይቀሰቅሳሉ፡፡ The Signs of the Times, January 19,1882. MYPAmh 59.5