Go to full page →

ከተጠራጣሪዎች ጋር ህብረት የመፍጠር አደጋ MYPAmh 61

በፍትወት በተቃጠለ ዓለም ውስጥ እየኖርን ነን፡፡ ወጣቶችና ጎልማሶች በኃጢአት ደፋሮች ናቸው፡፡ ወጣቶቻችን በቅድስና ካልተጠበቁ በስተቀር፤ በፅኑ መርሆዎች ካልተገነቡ በስተቀር፣ ጓደኞችንና አእምሮን የሚመግበውን ሥነ ፅሁፍ በመምረጥ ረገድ ታላቅ ጥንቃቄ ካልተደረገ በስተቀር ልክ እንደ ሶዶም ኗሪዎች የሞራል ውድቀት ላለባቸው ህብረተሰብ የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡ የዓለም ህዝብ ውጫዊ ገፅታው በጣም ማሪኪ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሁል ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መጥፎ አስተያየት የሚወረውሩ ከሆኑ በጣም አደገኛ ወዳጆች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የእምነታችሁን መሰረት ዝቅ ለማድረግና የጥንቱን የወንጌል እምነት ትክክለኛነት ለማበላሸት ሁል ጊዜ ስለሚሹ ነው፡፡ MYPAmh 61.3

ወጣቶች ብዙ ጊዜ የመጠራጠር ዝንባሌ ካላቸው ጋር ይገናኛሉ፡፡ አሰቃቂ የሆነው የክፋት ሥራ እስኪፈፀምና ወጣቶቹን እስኪያጠፋቸው ድረስ ወላጆቻቸው እውነታውን አያውቁትም፡፡ ወጣቶች የእነዚህን ሰዎች እውነተኛ ባሕርይ በተመለከተ እንዳይታለሉ፣ ከእነርሱ ጋር ጓደኝነት እንዳይፈጥሩና የእነዚህ ሰዎችን የማሾፍና ለማታለል የታቀደ ሀሰተኛ ክርክር እንዳይሰሙ በትጋት ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ወጣቶቻችን የእነዚህን ሰዎች አለማመን በሚገነዘቡበት ጊዜ ከእነርሱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማቋረጥ የሞራል ድፍረት ከሌላቸው በስተቀር በወጥመዱ ይጠመዱና ልክ እንደ ጓደኞቻቸው መናገርና የእነርሱን ድርጊት መፈፀም፣ ያውም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እምነት አቅልለው መናገር ይጀምራሉ፡፡ MYPAmh 61.4