Go to full page →

በእውነት ላይ መጠራጠርን በተመለከተ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ MYPAmh 61

ስለ ወጣቶቻችን እጅግ የጠለቀ ሃዘን ይሰማኛል፡፡ አደጋውን እንደ ማወቄ ካገኛችሁት ጥቂት የሳይንስ እውቀት የተነሳ ራሳችሁ በሰይጣን ወጥመድ እንዳትጠመዱ አስጠነቅቃችኋለሁ፡፡ ያለ ፈርሃ-እግዚአብሔር ልታገኘው ከምትችለው እውቀት ሁሉ ይልቅ ንፁህና ትሁት ልብ ያለህ መሆን ይሻላል፡፡ MYPAmh 61.1

የዛሬ ወጣቶች የትም ቢሄዱ ተጠራጣሪዎችንና አረመኔዎችን የመገናኘት አጋጣሚ ስላላቸው ስለሚያምኑት ተስፋ በገርነትና በፍርሃት ማብራሪያ መስጠት እንዲችሉ በበቂ ሁኔታ የታጠቁ መሆን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ቶማስ ፔይን ሞቶ በመቃብር ውስጥ ያለ ቢሆንም ሥራዎቹ በዓለም •ርግማን ሆነው ይኖራሉ፡፡ ዛሬም የእግዚአብሔርን ቃል እውነት የሚጠራጠሩ፣ እነዚህን የአረመኔነት ውጤቶችን ልምድ በሌላቸው ወጣቶች እጅ በማስቀመጥ ልባቸውን መርዘኛ በሆነ የጥርጣሬ ከባቢ አየር ይሞላሉ፡፡ የሰይጣን መንፈስ ነፍሳትን የማጥፋት ስልቱን ለማሳካት በክፉ ሰዎች ውስጥ ይሰራል፡፡ MYPAmh 61.2