Go to full page →

የሞራል ድፍረት ያስፈልጋል MYPAmh 62

ወጣቶቻችን ፈተና በየአቅጣጫው ስለሚያገኛቸው በሟቾች ከሚሰጥ ኃይልና ትምህርት በበለጠ ከፍ ያለ ኃይልና ትምህርት መደገፍ እንዳለባቸው ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ በየቦታው እግዚአብሔርን የሚንቁና በተለምዶ በክርስትና ላይ የንቀት ቃላት የሚወረውሩ አሉ፡፡ ያልተማሩ ሰዎችን በቀላሉ ለማሳመን የተፈለሰፈ የህፃናት መጫወቻ ነው ብለው ይጠሩታል፡፡ MYPAmh 62.4

የሞራል ኃይል የሌላቸው እውነትን ከጥቃት መከላከል አይችሉም፡፡ «እንደዚህ ዓይነት ንግግር ካላቆማችሁ በስተቀር ከናንተ ጋር አብሬ መሆን አልችልም፡፡ የሱስ የዓለም መድህን ለኔ አዳኜ ነው፡፡ የዘላለም ህይወት ተስፋዬ የተማከለው በእርሱ ነው፡፡» ለማለት ድፍረት የላቸውም፡፡ ነገር ግን እንደ እነዚህ ዓይነቶቹን ዝም የማሰኘት ብቸኛ ዘዴ ይህ ነው፡፡ ከተከራከራችኋቸው የሚጋፈጡአችሁ የመከራከሪያ ነጥቦች ስላሉአቸው ማንኛውም የምትነግሩአቸው ነገር አይነካቸውም፡፡ ነገር ግን ለክርስቶስ ከኖራችሁ፣ ከሰማይ አምላክ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ጥብቅ ከሆነ ክርክር ሊያደርግ ያልቻለውን ነገር ታደርጉላቸውና እግዚአብሔርን በመምሰል ኃይል የፍልስፍናቸውን ስህተትነት ታሳምኑአቸዋላችሁ፡፡ MYPAmh 62.5

በክርስቶስ ደም የተገዙ፣ እግዚአብሔርን እንዲያከብሩበት መክሊቶች የተሰጡአቸው፣ የክርስቶስን መለኮትነት በመካድና በራሳቸው ውስን የማሰብ ችሎታ በመታመን፣ እንዲሁም መሰረት የሌላቸውን መከራከሪያዎች በመያዝ በእግዚአብሔር ፀጋ በተላከላቸው መልእክት ለማሾፍ ሲመለሱ ከማየት የበለጠ አሳዛኝ የሆነ ነገር የለም፡፡ በመከራ ሲፈተኑና ከሞት ጋር ፊት ለፊት ሲፋጠጡ የነበሩአቸው እነዚህ የሀሰት እምነቶች በፀሐይ ፊት እንደሚቀልጥ ጤዛ ይቀልጣሉ፡፡ MYPAmh 62.6

የእግዚአብሔርን የምህረት ተማጽኖ እምቢ ባለ ግለሰብ የሬሳ ሳጥን አጠገብ መቆም ምንኛ አሳቃቂ ነው! እዚህ የጠፋ ነፍስ አለ ማለት ምንኛ አሰቃቂ ነው! ከፍ ወዳለው ደረጃ መድረስና የዘላለም ሕይወት ማግኘት የሚችል ሰው ሕይወቱን ለሰይጣን አሳልፎ በመስጠት፣ በከንቱ የሰዎች ፍልስፍናዎች በመጠመድና የክፉው መጫወቻ ሆኖ ማየት ምንኛ አሰቃቂ ነው! የክርስቲያን ተስፋ ለነፍስ እንደ መልሕቅ ነው፤ እርግጠኛና የጸና ሰው ክርስቶስ የበኩር ሆኖ ለኛ ወደ ገባበት ከመጋረጃ ውስጥ የሚገባ ነው፡፡ ከፊታችን ላሉ ታላላቅ ክስተቶች ለመዘጋጀት ማድረግ ያለብን የየግላችን ስራ አለን፡፡ MYPAmh 63.1