Go to full page →

አንዲት ደካማ ነጥብ MYPAmh 64

ሌሎች ከሚፈጽሙት ብዙ •ኃጢአቶች ነፃ ነን በማለት ራሳችንን እናታልል ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጠንካራ ጎኖች እያሉን አንድ ደካማ ጎን ካለን አሁንም ነፍስና ኃጢአት ግንኙነት አላቸው ማለት ነው፡፡ ልብ በአገልግሎቱ የተከፋፈለ ስለሆነ «ግማሽ የራሴ ግማሽ ደግሞ ያንተ” ይላል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ከዚህ በፊት ይንከባከበውና ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ፈልጎ በማግኘት እግዚአብሔር ከልቡ እንዲቆርጥለት መፍቀድ አለበት፡፡ በእግዚአብሔር እይታ ከባድ ስለሆነ ያንን አንድ ኃጢአት ማሸነፍ አለበት፡፡ MYPAmh 64.1

አንዱ «እኔ ከሌሎች ያነስሁ ቀናተኛ አይደለሁም፣ ነገር ግን ምንም እንኳን ቁጣዬን መቆጣጠር ባለመቻሌ ሁል ጊዜ ባዝንም ለመናገር እገደድና መጥፎ ነገሮችን እናገራለሁ» ይላል፡፡ ሌላኛው ደግሞ «እኔ ይህኛው ወይም ያኛው ስህተት አለብኝ፡፡ ነገር ግን እኔ በማውቃቸው አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚታየውን ይህንና ይህን የሚመስሉ ጥፋቶችን በጣም እጠላለሁ” ይላል፡፡ አንዳንድ ኃጢአቶችን ትንሽ ውጤት ስላላቸው የሚያስከትሉት ጉዳት አነስተኛ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ትልልቅ ስለ ሆኑ ብዙ ጉዳት ያስከትላሉ በማለት •እንድንመድብ እግዚአብሔር ደረጃ የሰጣቸውን የኃጢአቶች ዝርዝር አልሰጠንም፡፡ MYPAmh 64.2

የአንድ ሰንሰለት ጥንካሬው ከአንድ ደካማ መገናኛ ቦታው የበለጠ አይደለም፡፡ ይህን ሰንሰለት በአጠቃላይ ሲታይ ጥሩ ነው ልንል እንችላለን፣ ነገር ግን አንዱ የሰንሰለት መገናኛ ቁልፉ ደካማ ከሆነ ያ ሰንሰለት እምነት የሚጣልበት አይደለም፡፡ የማሸነፍ ሥራ ወደ እግዚአብሔር መንግስት የሚገባ የእያንዳንዱ ነፍስ ሥራ መሆን አለበት፡፡ ከከንፈራችሁ ሊወጡ እየተርገበገቡ ያሉ ትዕግስት የጎደላቸው ቃላት ከአፋችሁ ሳይወጡ መቅረት አለባቸው፡፡ ባሕርያችሁ በትክክል ያልተገመተበት አስተሳሰብ ከእናንተ መወገድ አለበት፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በሌሎች ላይ የሚኖራችሁን መልካም ተጽእኖ ስለሚያዳክምባችሁና በሌሎች አእምሮ ዝቅተኛ ግምት ስለሚያሰጣችሁ ነው፡፡ እናንተ ሰማዕታት እንደሆናችሁ የመቁጠርን ሀሳብ በማሸነፍ « ጸጋዬ ይበቃሃል” ያለውን የክርስቶስ ተስፋ ያዙ፡፡ Review and Herald, August 1,1893. MYPAmh 64.3