Go to full page →

በየእለቱ በእግዚአብሔር መደገፍ MYPAmh 63

ጧት ከመኝታህ ስትነሳ ረዳት የለሽነትህና ከእግዚአብሔር ብርታት እንደሚያስፈልግህ ይሰማሃልን? እናም ለሰማዩ አባትህ ከልብህ ሆነህ በትህትና ፍላጎትህን ታሳውቃለህን? እንደዚህ ከሆነ መላእክት ፀሎትህን በአጽንኦት ይመለከቱታል፡፡ እነዚህ ፀሎቶች ከማያስመስሉ ከንፈሮች ከሆነ ባለማወቅ ስህተት የመሥራት አደጋ ውስጥ ስትሆንና ሌሎችን ስህተት እንዲሰሩ የሚያደርግ ተጽእኖ እያሳደርክባቸው ቢሆን ጠባቂ መልአክህ በተሸለ አቅጣጫ በማደፋፈር ፣ ላንተ ቃላቶችህን በመምረጥና በድርጊትህ ላይ ተጽእኖ በማሳደር ከጎንህ ይሆናል፡፡ MYPAmh 63.3

በአደጋ ውስጥ መሆንህ የማይሰማህ ከሆነና ፈተናን ለመቋቋም እርዳታና ብርታት እንዲሰጥህ የማትፀልይ ከሆንክ ወደ ስህተት ልትመራ እንደምትችል እርግጠኛ ሁን፡፡ ተግባርህን ችላ ማለትህ በሰማይ ባለው በእግዚአብሔር መጽሐፍ ይፃፋል፤ በፈተናው ቀን ተመዝነህ ቀለህ ትገኛለህ፡፡ Testimonies for the church, vol.3,p 363 — 364. MYPAmh 63.4