Go to full page →

ፍፁም ባህሪይን መመስረት MYPAmh 68

የባህሪይ ፍፅምና ደረጃ ላይ መድረስ ቀላል ነገር ነው የሚል ማረጋገጫ ክርስቶስ አልሰጠንም፡፡ የከበረ የተሟላ ባህሪይ በውርስ አይገኝም፡፡ በአጋጣሚ የሚመጣም አይደለም፡፡ የከበረ ባህሪይ በክርስቶስ በተደረገው መልካም ሥራና ፀጋ አማካይነት በግለሰቡ ጥረት የሚገኝ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔር መክሊቶችንና የአእምሮ ኃይሎችን ይሰጣል፡፡ እኛ ዳግሞ ባህሪይን እንመሰርታለን:: ባህሪይ የሚመሰረተው ከራስ ጋር ጠንካራና ጥብቅ ጦርነት በመግጠም ነው፡፡ በውርስ ካገኘናቸው ዝንባሌዎቻችን ጋር ተከታታይ ጦርነቶች መደረግ አለባቸው፡፡ ራሳችንን በቅርብ ሂስ እየሰጠነው አንድም ቢሆን መጥፎ ባህሪይ ሳይታረም እዲቀር መፍቀድ የለብንም፡፡ MYPAmh 68.1

ማንም ሰው እኔ የባህሪይ ጉድለቶችን ማስተካከል አልችልም አይበል፡፡ ወደዚህ ውሳኔ ከደረሳችሁ በእርግጠኝነት የዘላለምን ሕይወት ታጣላችሁ፡፡ ያለመቻል ያለው በራሳችሁ ፈቃድ ላይ ነው፡፡ ፈቃደኛ ካልሆናችሁ አሸናፊዎች መሆን አትችሉም፡፡ የትክክለኛው ችግር መነሻው ካልተቀደሰ ልብ ክፋትና ለእግዚአብሔር ቁጥጥር ራስን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ነው፡፡ MYPAmh 68.2