Go to full page →

ሕያው እምነት MYPAmh 70

ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት ስለማይቻል የክርስቶስ ተከታይ በልብ ውስጥ የፀና እምነት ሊኖረው ይገባል፡፡ እምነት ዘላለማዊ እርዳታን የሚይዝ እጅ ነው፤ አዲስ የሆነው ልብ ከክርስቶስ ልብ ጋር አብሮ የሚመታበት ማዕከል ነው፡፡ MYPAmh 70.3

ንስር ቤትዋን ለመድረስ በምታደርገው ጥረት ብዙ ጊዜ በወጀቡ ኃይል ወደ ጠባቡ የተራራ ሸለቆዎች ትወረወራለች፡፡ ደመናዎች ጠቁረውና ቁጡ ቁልል ሰርተው በእርስዋና ጎጆዋን ከሰራችበት ፀሐያማ ከፍታዎች መካከል ይሄዳሉ፡፡ ለአንድ አፍታ ንስርዋ ግራ የተጋባች በመምሰል እነዚያን ጥቁር ደመናዎች ወደ ኋላዋ የምትጠርግ ይመስል ጠንካራ ክንፎችዋን በማርገብገብ ወዲያና ወዲህ ትበራለች፡፡ ከእሥር ቤትዋ ነፃ የምትወጣበትን መንገድ ለማግኘት በምታደርገው ከንቱ ጥረት በምታሰማው ያልተለመደ ጩኸት የተራራ እርግቦችን ታባንናቸዋለች፡፡ በመጨረሻ በጨለማው ውስጥ ወደ ላይ በኃይል ትቀዝፍና ከአፍታ በኋላ ከላይ ካለው ፀጥ ያለ የፀሐይ ብርሃን ካለበት ብቅ ስትል ድልን የሚያበስር የፉጨት ጩኸት ታሰማለች፡፡ ጨለማውና ወጀቡ ከበታችዋ ቀርተው በዙሪያዋ የሰማይ ብርሐን ያበራላታል፡፡ እጅግ ከፍ ብሎ ባለው በአለት ንቃቃት ወዳለው ተወዳጁ ቤትዋ በመድረስ ትረካለች፡፡ ይህንን ማድረግ ከፍተኛ ጥረት የጠየቃት(ዋጋ ያስከፈላት) ቢሆንም የፈለገችውን ዓላማ በማሳካትዋ ዋጋዋን አግኝታለች፡፡ MYPAmh 70.4

እንደ ክርስቶስ ተከታዮች እኛም መከተል ያለብን መንገድ ይህ ነው፡፡ እንደ ወፍራም ግንብ እኛን ከሰማያዊ ብርሐን የሚለዩንን ደመናዎች ጥሶ የሚያልፍ ህያው እምነትን መለማመድ ያስፈልገናል፡፡ ሁሉም ነገር በመንፈስ ቅዱስ ሰላምና ደስታ የሆነበት ልንደርስባቸው የሚገባ የእምነት ከፍታዎች አሉ፡፡ MYPAmh 70.5