Go to full page →

የእምነት ገድል MYPAmh 70

ከወጣቶች ውስጥ አብዛኞቹ እግዚአብሔርን ለማገልገል የተወሰነ መርህ የላቸውም፡፡ በእያንዳንዱ ደመና ሥር ይሰምጣሉ፤ ችግርን የመቋቋም ኃይል የላቸውም፡፡ በፀጋ አያድጉም፡፡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁ ይመስላሉ፤ ነገር ግን ለህጉ ተገዥ አይደሉም፤ ሊሆኑም አይችሉም፡፡ ሥጋዊ ልባቸው መለወጥ አለበት:: በቅድስና ውስጥ ያለውን ውበት ማየት አለባቸው:: ያኔ ዋልያ ወደ ውሃ ምንጮች እንደሚናፍቅ ቅድስናን ይናፍቃሉ፡፡ ያኔ የክርስቶስ ቀንበር ልዝብና ሸክሙም ቀላል ይሆንላቸዋል፡፡ MYPAmh 70.1

ውድ ወጣቶች ሆይ ጉዞአችሁ በጌታ ትዕዛዝ የሚከናወን ከሆነ መንገዳችሁ ሁል ጊዜ ውጫዊ ሰላምና ብልጽግና ያለው እንዲሆን አትጠብቁ፡፡ ወደ ዘላለማዊው ቀን የሚያመራው መንገድ ለመጓዝ ቀላል አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ እሾሃማና ጨለማ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ክንዶች ከክፉ ሊከላከሉላችሁ እንደሚከቡአችሁ ማረጋገጫ አለላችሁ፡፡ በእርሱ የፀና እምነት እንዲኖራችሁና በጥላ ውስጥም ሆነ በፀሐይ ብርሃን ውስጥ በእርሱ መታመንን እንድትማሩ ይፈልግባችኋል፡፡ MYPAmh 70.2