Go to full page →

ድል የነሣው ሕይወት MYPAmh 74

ሰላም የሚመጣው በእግዚአብሔር ኃይል ላይ በማረፍ ነው። ነፍስ በተሰጠው ብርሃን መሰረት ተግባሩን ለመፈፀም እንደወሰነ ወዲያውኑ መንፈስ ቅዱስ ተጨማሪ ብርሃንና ብርታት ይሰጣል። የመንፈስ ፀጋ ከነፍስ ውሳኔ ጋር አብሮ እንዲሰራ ይሰጣል፡ ነገር ግን ለግለሰቡ የእምነት ልምምድ መተኪያ አይሆንም። በክርስቲያን ሕይወት ስኬት የሚገኘው እግዚአብሔር የሰጠውን ብርሃን በመቀበል ነው። ነፍስን በክርስቶስ ነፃ ማድረግ የሚችለው የብርሃኑና የመረጃው ብዛት አይደለም ። ነገር ግን የነፍስ ኃይሎች ፈቃድና ጉልበቶች «ጌታ ሆይ እኔ አምናለሁ፡ አለማመኔን እርዳው» በማለት ከልብ ለመጮህ ሲነሱ ነው ስኬት የሚገኘው። MYPAmh 74.1

እኔ ለወደፊቱ ስኬት ባለው ብሩህ ተስፋ ደስ ይለኛል፣ እናንተም እንደዚሁ ሊሰማችሁ ይችላል። ደስ ይበላችሁ፣ ጌታን ለፍቅር ርህራሄው አወድሱት። እናንተ የማታስተውሉትን ለእርሱ አሳልፋችሁ ስጡ። ይወዳችኋል:: በእያንዳንዱ ድክመታችሁም ያዝንላችኋል። እርሱ «በሰማያዊ ሥፍራዎች በክርስቶስ ባሉ መንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ ባርኮናል።» ዘላለማዊ የሆነው አምላክ ልብ ልጁን ለሚወዱት ለልጁ ከሚሰጣቸው በረከቶች ያነሰ በረከት በመስጠት አይረካም። MYPAmh 74.2

ሰይጣን አእምሮአችንን ከኃያሉ ረዳታችን ለማራቅና በነፍስ ውድቀታችን ላይ እንድናሰላስል ሊመራን ይሻል። ነገር ግን ኢየሱስ ያለፈውን ኃጢአታችንን የሚያይ ቢሆንም ምህረትን ይሰጠናል። ስለሆነም ፍቅሩን በመጠራጠር አናዋርደው። የበደለኝነት ስሜት በመስቀሉ ሥር ካልተጣለ በስተቀር የሕይወትን ምንጮች ይመርዛል። ሰይጣን ማስፈራሪያዎቹን ሲሰድብህ ከእነርሱ ፊትህን አዙርና በእግዚአብሔር ተስፋዎች ነፍስህን አፅናና። ደመና በራሱ ጨለማ ቢሆንም በሰማያዊ ብርሃን ሲሞላ ግን የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያርፍበት ወደ ወርቃማ ብሩህነት ይለውጠዋል። MYPAmh 74.3

የእግዚአብሔር ልጆች የስሜቶች ተገዥ መሆን የለባቸውም። በተስፋና በፍርሃት መካከል ሲዋዥቁ የክርስቶስ ልብ ይቆስላል። ለዚህም ምክንያቱ የማይሳሳት የፍቅሩን ማረጋገጫ ስለሰጣቸው ነው። እርሱ የሰጣቸውን ሥራ እንዲሰሩ ይፈልግባቸዋል። ያኔ ልባቸው በእጁ እንደ ቅዱስ በገና ይሆንና እያንዳንዱ ምት የዓለምን ኃጢአት እንዲያስወግድ ለተላከው ምስጋናና ውዳሴ የሚያመነጭ ይሆናል። MYPAmh 74.4

ክርስቶስ ለልጆቹ ያለው ፍቅር ብርቱ የመሆኑን ያህል ርህሩህም ነው። ፍቅሩ ከሞት ይልቅ የበረታ ነው። ምክንያቱም የእኛን መዳን ለመግዛትና ከራሱ ጋር ምስጢራዊና ዘላለማዊ በሆነ መንገድ አንድ ሊያደርገን ሞተልን:: ፍቅሩ እጅግ ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ የእርሱን ኃይሎች በሙሉ ይቆጣጠርና ሰፊ የሆነ የሰማይ ግብአቶችን ለእግዚአብሔር ህዝብ ጥቅም ያውላል። በእርሱ ዘንድ መለያየትና የመመለስ ጥላ የሌለበት ነው፤ ትናንትም ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው። ምንም እንኳን ኃጢአት የእግዚአብሔርን ፍቅር በመቃወምና ወደ ምድር እንዳይፈስ እንቅፋት እየሆነ ለዘመናት ቢኖርም፣ ክርስቶስ ለሞተላቸው አሁንም ቢሆን በበለፀጉ ስርፀቶች በመፍሰስ ላይ ይገኛል።—Testimonies to Ministers, 518-519. MYPAmh 74.5