Go to full page →

በንስሐ የሚገኝ ደስታ MYPAmh 73

ለሰው የመዳኛ ሁኔታዎች በእግዚአብሔር የታዘዙ ናቸው። ራስን ማዋረድና መስቀልን መሸከም ተናዛዡ ኃጢአተኛ መፅናናትና ሰላም እንዲያገኝ የተሰጡ ነገሮች ናቸው። ሰው ለመቼም ቢሆን እንዲሸከመው ሊጠራ ለማይችለው ውርደትና መስዋዕትነት ኢየሱስ ራሱን መስጠቱ እያንዳንዱን ማጉረምረም ፀጥ ማድረግ አለበት። ለሰው ጣፋጭ ደስታ ሊመጣለት የሚችለው ሕጉን በመተላለፉ ለእግዚአብሔር ከልቡ ሲናዘዝና ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአተኞች አዳኝና ጠበቃ መሆኑን ሲያምን ነው። The Signs of the Times, March 4, 1880 MYPAmh 73.6