Go to full page →

ጥሪ ለወጣቶች MYPAmh 22

እግዚአብሔር ወጣቶችን ትጉህ አእምሮ ያላቸው፣ በከበረው ስራው ለተግባር የተዘጋጁና ሃላፊነትን ለመሸከም ገጣሚዎች እንዲሆኑ ይፈልጋል:: እግዚአብሄር ያልረከሰ ልብ ያላቸውን፣ ብርቱና ደፋር የሆኑ፣ ከፊታቸው ያለውን ጦርነት እንደ ጀግና ወንድ ለመዋጋት የወሰኑ፤ በዚህ ድርጊታቸውም እግዚአብሔን የሚያከብሩና ሰብዓዊ ዘርን የሚባርኩ ወንዶችን ይፈልጋል:: ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን ቢያጠኑ፣ ችኩል ፍላጎታቸውን መቆጣጠር ቢችሉና የፈጣሪያቸውንና የአዳኛቸውን ድምፅ ማድመጥ ቢችሉ ኖሮ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም መፍጠር ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ከብረውና ከፍ ከፍ ብለው ያገኙት ነበር:: ወጣት ወዳጄ ሆይ! ሊገመት ከሚችል በላይ ጠቀሜታ ላለው የእግዚአብሔር ቃል መመሪያ ራስህን መስጠት ላንተው ለዘላለማዊ ሕይወት ጥቅም ነው:: MYPAmh 22.1

ብልህ እንድትሆን፣ ከእግዚአብሄር መንፈስ ቁጥጥር ውጭ የሆነና ያልተገራ ህይወትን መምራት ምን እንደሚሆን እንድታስብ አደፋፍርሃለሁ:: «አትሳቱ፣ እግዚአብሄር አይዘበትበትም:: ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል:: ስጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ ከሥጋው ጥፋትን ያጭዳል:: መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ህይወት ያጭዳል::» ለነፍስህ ብለህ፣ ህይወትህን ከጥፋት ለማዳን ራሱን ለሰጠ ለየሱስ ብለህ በህይወትህ ጅምር ላይ ቆመህ ሃላፊነቶችን፣ የተሰጡህን እድሎች፣ ልታደርጋቸው የምትችላቸውን ነገሮች በደንብ መዝን:: እግዚአብሔር ከፍ ያለ መዳረሻን እንድትሞላ እድል ሰጥቶሃል:: የምታሳድረው ተጽዕኖ ለእግዚአብሔር እውነት ሊናገር ይችል ይሆናል:: በሰብዓዊ ዘር ደህንነት ትልቅ ሥራ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር አብረህ ሠራተኛ ልትሆን ትችላለህ:: MYPAmh 22.2